የጀርመን ምክር ቤት የኮምፕዩተር ስለላ
ሐሙስ፣ ሰኔ 4 2007ማስታወቂያ
የሀገሪቱን የመገናኛ አዉታሮች የሚጠብቀዉ ክፍል ከእንግዲህ እንዲህ ያለዉን የሳይበር ጥቃት መክቶ መከላከሉን አቁሞ ኮምፕዩተሮቹን ጠቅላላ ነቅሎ በአዲስ ተክቶ ፕሮግራሞችንም በሌላ መተካት ይገባል ከሚል ዉሳኔ ላይ መድረሱ ተሰምቷል። ዛሬ በርሊን ላይ እንደተነገረዉ የጀርመን ሸንጎ አባሎችና የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ምስጢርና ሰነድ መጠለፉ አስቀድሞም ተደርሶበት ነበር። ከጀርባዉ ትልቅ የስለላ ድርጅት ስለመኖሩ ከመነገሩ ዉጭ ግን ማንነቱም ሆነ የደረሰዉ የጥፋት መጠን በሰፊዉ አልታወቀም። ይልማ ኃይለሚካኤል ከበርሊን ዝርዝር ዘገባ አለዉ
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ