1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ሴቶችና የሚፀፈምባቸው ጥቃት

ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2002

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ህዳር 25 በኛ ህዳር 16 በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዲቆሙ በዓለም ዙሪያ ጥሪ የሚተላለፍበት ዕለት ነው ። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታሰበው ይህ ዕለት በጀርመንም ተመሳሳይ ትኩረት ይሰጠዋል ።

https://p.dw.com/p/Kg9v
ምስል dpa

ምንም እንኳን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በአመዛኙ በደሀዎቹ አገራት ብቻ የሚደርሱ ተደርገው ቢወሰዱም ፣ ችግሩ ግን እንደ ጀርመን ያሉ የበለፀጉ አገራት ሴቶችም የሚጋሩት አሳዛኝ ዕውነታ ነው ። ጀርመን የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን የሚደግፍ ህግ ያላት ሲሆን በርካታ ማህበራዊ ድርጅቶችም ለተጠቂዎቹ ይቆማሉ ።

ፔትራ ኒክሊስ ፣ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ