1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ቋንቋና የዉጭ አገር ዜጎች

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2008

ስደተኞች የመኖርያ ፈቃድ ሲያገኙ የጀርመን መንግሥት ወጪውን ችሎ ለስድስት ወራት ጀርመንኛ ይማራሉ ። የጀርመን ቋንቋ ማወቃቸዉ ከኅብረተሰቡ ጋር ቶሎ እንዲቀላቀሉ ይረዳቸዋል።

https://p.dw.com/p/1HRus
Sprachkurs für Flüchtlinge aus Syrien Eritrea Iran Irak Deutschkurs Deutsch lernen
ምስል picture-alliance/dpa/H.Schmidt

[No title]

ከእስያ ከላቲን አሜሪካ ከመካከለኛዉ ምስራቅና ከአፍሪቃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጀርመን እየመጡ ተገን ይጠይቃሉ። ስደተኞች የመኖርያ ፈቃድ ሲያገኙ የጀርመን መንግሥት ወጪውን ችሎ ለስድስት ወራት ጀርመንኛ ይማራሉ። ቋንቋውን ማወቃቸዉ ከኅብረተሰቡ ጋር ቶሎ እንዲቀላቀሉ ይረዳቸዋል። ፍራንክፈርት ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ሆፍ ኃይም ከተማ ከአፍጋኒስታን፤ ከፓኪስታን፤ ከኢራን ከኢራቅ፤ ከሶርያ፤ ከሶማልያ፤ ከኤርትራና ኢትዮጵያ የመጡ በርካታ ስደተኞች ይገኛሉ። ከስደተኞቹ ገሚሱ የጀርመንን አገር የመኖርያ ፈቃድ ያገኙ ናቸዉ።የተቀሩት ደግሞ የመኖርያ ፈቃድ እስኪሰጣቸዉ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።የፍራንክፈርት ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን ሆፍ ኃይም በሚገኘዉ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል ከኢትዮጵያ፤ ከኤርትራ እንዲሁም ከአፍጋኒስታን የመጡ ዜጎችንና የቋንቋ መምህራንን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ጎይቶም ቢሆን

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ