1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ባህል ነክ ጥንቅሮች

ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2003

በሰሜን አፍሪቃዋ አገር በቱኒዝያ የጀመረዉ የዲሞክራሴ ንቅናቄ በቀጣይ የግብጽ ፕሪዝደንት ሆስኒ ሙባረክን የሰላሳ አመት በላይ የስልጣን ዘመን አስወግዶ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የግብጽ ህዝብ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ ድምጽ ሲሰጥ ዉሎአል።

https://p.dw.com/p/RCDE
የጀርመን የሴቶች የጃዝ ሙዚቃ ቡድንምስል Goethe Institut

ህዝባዊ አብዮቱ ከጀመረ ከሰባት ሳምንት ወዲህ ታድያ በግብጽ ይታይ የነበረዉ ጠንካራ ባህል ነክ እንቅስቃሴ ተዳፍኖ ቆይቶ ለመጀመርያ ግዜ ሙዚቃና እና አብዮት በሚል መርህ በመዲናዋ ካይሮ ታላቅ የጃዝ ሙዚቃ መካሄዱን የባህል ድረ-ገጾች ሲዘግቡ ሰንብተዋል፣ እኛም ዛሪ በለቱ የምንዳስሰዉ አንዱ ርእሳችን ነዉ። ሌላዉ ጀርመን ምስራቃዊ ከተማ በላይፕዚግ አመታዊዉ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ስለመካሄዱ እና እንዲሁም ደን የህይወት መገለጫ የባህል ማሳያ አንዱ መድረክ በመሆኑ የያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም አለም አቀፍ የደን-አመት በመባል መሰየሙን በማስመልከት የያዝነዉ አጠር ያለ ዘገባ በለቱ የባህል መድረካችን ተካቶአል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

በምስራቅ ጀርመን በምትገኘዉ በላይፕዚግ ከተማ በያመቱ የሚካሄደዉ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ በዘንድሮ ዝግጅቱ ከምንግዜዉም በላይ በርካታ አንባብያንን እና ጎብኝዎን ማስተናገዱ ተገልጾአል። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ የተለያዩ የልብ ወለድ፣ የህጻናት እንዲሁም ለወጣት አንባብያን በየአዕድሜያቸዉ ተስማሚ መጻህፍትን እንዲሁም ከባልካን አገራት ልዪ ልዪ የስነ-ጽሁፍ ስራዎችን በማቅረብ በአጠቃላይ በመቶ ስድሳ ሶስት ሽህ የስነ-ጽሁፍ አድናቂዎች በመጎብኘቱ ቀዳሚዉን ስፍራ መያዙ ተነግሮለታል። በተለይም ባለፈዉ ቅዳሜ በእግዚቢሽኑ የቀረቡትን መጻህፍት ለመጎብኘት የመጣዉ ህዝብ እጅግ ብዙ እንደ ነበር እና በቦታዉ ላይ ጠጥር መጣያ እንዳልነበር ተመልክቶአል። ከአዉደ ርዕዪ ጎብኝዎች መካከል በተለይ የኩምክና ትረካን የሚያጠቃልሉ መጻህፍትን የሚያፈቅሩ ህጻናት እና ወጣቶች ይገኙበታል። የተዋጣለት ስራን የሆነዉ በቀን የሶስት የአራት ሰአት እንቅልፍ ብቻ ኖሮን ነዉ የሚሉት የመጽሃፍት እግዝቢሽኑ ተጥሪ ኦሊቨር ሲለ በአዉደ ርዕዪ ከተገኙት የተለያዩ የመጽሃፍ አሳታሚ ድርጅቶች፣ እና ጸሃፍ ጋር በመነጋገር፣ በእግዝቢሽኑ ላይ ከሚደረጉ በተለያዩ የትረካ ፕሮግራሞች ላይ በመገኝት እና ከደራስያን ጋር የተለያዪ ዉሎችን በመፈጸም ነዉ።
«በጣም የተዋጣለት የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ በመሆኑ ተደስቻለሁ። የተዋጣለት ስንል፣ አዉደ ርዕዩን የጎበኘዉን የህዝብ ብዛት እና የደረሰንን መልካም አስተያየት መዘርዝሮች ገምግመን ያገኘነዉን መልስ በመመልከት ነዉ። በርግጥ የትርኢቱ መጠናቀቅያ እለት የአካባቢዉ የተፈጥሮ ሁኔታም የተዋጣለት ሚና ተጫዉቶአል ማለት ያስችላል፧ ብራማ እና ድምቅ ያለ ጸሃይ የፈነጠቀበትም ቀን ነበር። ታድያ ይህን እጅግ ሰፊ የሆነ አዉደ ርእይ ለአራት ቀናት እይታ ስንዘረጋ ቀን ከለሊት ሰርተናል፣ በስራ መረሃ-ግብራችንም መሰረት የተዋጣለት ዉጤት በማግኘታችን እድለኞች ነን»
የማንበብ ባህልን ከልጅነት የሚጀምሩት ጀርመናዉያን በአገር ዉስጥ አዲስ የታተሙ መጽሃፍትን ለማወቅ ታዋቂ እና የተዋጣላቸዉ ደራስያን የተባሉትንም ልምድ እና ስራ ለመተዋወቅ በየግዜዉ የተለያየ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ይካሄዳል። በተለይም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁት የፍራንክፈርቱ እና ለሶስት ቀናት የዘለቀዉ እና ባለፈዉ እሁድ እለት የተጠናቀዉ የላፕዚጉ አለም አቀፍ የመጽሃፍ አዉደ ርእይ ነዉ። በዚህ የመጽሃፍ እግዚቢሽን ላይ ከአገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በአመቱ አልያም በወቅቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን ያገኙ መጻህፍት እና ጻህፍት መተዋወቅያም መድረክ ነዉ። አንደ እግዚቢሽኑ ተጠሪ ገለጻ ማንጋ የተሰኝዉን የጃፓን የህጻናት የኩምክና መጽሃፍ እንዲሁም የህጻናት መማርያ መጻህፍት በብዛት ይገኙበታል።
«በመጽሃፍ አዉደ ርዕዩ ከሚታዪት መጽሃፍት መካከል የትምህርት መጻህፍት ቁጥር ብዛት ጨምሮአል። ያ ማለት በዘንድሮዉ የላይፕዚግ መጽሃፍ አዉደ ርዕይ ላይ ከሃያ ሽህ በላይ የመማርያ መጻህፍት ቀርበዋል። ይህ ማለት የመጻህፍ ትርኢቱ ዉጤታማ እንደነበር እና የማንበብ ልምድ እና የብዙሃን መገናኛ ትምህርት ዘዴ፣ በመጻህፍት አዉደ ርዕዩ ላይ ይበልጥ በመጠናከር መቅረብ እንዳለበት ያሳየናል»
ዘንድሮ በላይፕዚጉ የመጽሃፍ ትርኢት የምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ አዉሮጻ አገራት የስነ-ጽሁፍ ስራ የቀዳሚነት ቦታ ይዘዉ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም የባልካን አገርዋ ሰርብያ ስነ-ጽሁፎች የላይፕዚጉ እግዚቢሽን በአለም አቀፍ ደረጃ መተዋወቅያ መንገድን ነዉ የፈጠረለት። የሰርቢያ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች ከይጎዝላቪያ ዉድቀት በኳላ ወደ በምዕራብ አዉሮጻ የጽሁፍ መድረክ ላይ ሲቀርብ ይህ የመጀመርያዉ ነበር። ሰላሳ ያህል የሰርቢያ የልብወለድ መጻህፍት በጀርመንኛ ተተርጉመዉ በእግዚቢሽኑ ቀርበዋል። በዚህ የመጽሃፍ አዉደ-ርዕይ ላይ አራባ የሰርብያ ጻህፍትን ተቀብለዉ በእግዚቢሽኑ ላይ ሲያስተናግዱ የነበሩት ማርያና ቪትማን አምስት ያህል የሰርቭያ ስነ-ጽሁፍ ወደ ጀርመንኛ ቋንቋ ተርጉመዋል
«ጥሩ እና ዉጤታማ የመጽሃፍ ትርኢት በመሆኑ ዘንድሮ በትርኢቱ ላይ ስነ-ጽሁፍን በማቅረብ ተካፋይ የነበረችዉ የሴርቢያ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች በሌላዉ አገራት በጥቂቱም ቢሆን ታዋቂነትን ያገኛሉ የሚል እምነት አለን። የስርቢያ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች በባልካን አገራት ጦርነት በነበረ ወቅት ተፈላጊነትን አግኘዉ ነበር። በጦርነቱ ወቅት ምን ይጻፋል በሚል ይመስላል በዝያን ሰአት ተፈላጊነቱ ጨምሮ የታየዉ። ልክ ጦርነቱ እንዳበቃ የሰርብያዉ ስነ-ጽሁፍ ተፈላጊነቱ በመቀነሱ ተገርሜ ነበር። በሌላ በኩል አሁን የሰርቢያዉ ስነ-ጽሁፍ በአንባብያን ዘንድ በድጋሚ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱ እዉን የሆነ ይመስለኛል»
በላይፕዚግ ከተማ የሚካሄደዉ አመታዊ አለማቀፍ የመጽሃፍ ትርኢት በስፋቱ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ከሚካሄደዉ አነስ ያለ ሁኖ የመጽሃፍ ትርኢት አነስ ያለ ሆኖ ሁለተኛ ደረጃነትን ቢይዝምም ዘንድሮ ለወጣት የሚሆኑ ልዮ ልዮ ስነ-ጽሁፎችን እና የትምህርት መጽሃፍትን በማቅረቡ ታላቅ አድናቆትን አግኝቶአል። በጀርመን በተለያዩ ግዝያት በሚደረገዉ የመጽሃፍ ትርኢት ጸሃፍትን በመጋበዝ የትምህርት ቤት መጽሃፍት እና ልምድን ለህዝብ እንዲያካፍሉ በማድረግ ማህበረሰቡ ከመጀመርያዉ ጀምሮ የማንበብ ባህል እንዲያዳብር የተለያየ ጥረትን ያደርጋሉ በሳምንቱ የባህል የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች በጀርመን የተካሄደዉን የመጽሃፍ አዉደርይ በተመለከተ በሰፊዉ ዘግበዋል።
ሌላዉ ሰሞኑን የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች ከዘገቡዋቸዉ ርዕሶች መካከል የያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም የደን ሃብት ጥበቃ አመት እንዲባል መሰየሙን በማስመልከት የደን ሃብት አንድ ህብረተሰብ ባህሉን ልምዱን የሚያሳይበትም ሆነ የሚቀስምበትም ቦታ መሆኑን ተገልጾአል። ጀርመናዉያን በረፍት ግዜያቸዉ ከቤተሰብ ጋር በመሆን ለሽርሽር በአካባብያቸዉ ወደ ሚገኝዉ ዘርዘር ወዳለ ጫካ በመሄድ ሽርሽር፣ የሩጫ ስፖርት፣ አልያም ከከተማ ወጣ ብሎ ነፋሻ አየርን የመቀበል ባህል አላቸሡ። በደን ዉስጥ አለፍ አለፍ ብሎ ለመዝናናት የመጣዉ ህብረተሰብ ጎኑን አረፍ የሚያደርግበትም መቀመጫ ብጤ ያበጃሉ የመጸዳጃ ቦታም ይሰራል። አንዳንድ ቦታ እንደዉም በተለይ በበጋዉ ወራት ጥቅጥቅ ባለ ደን ዉስጥ ኮረብታ ጫፍ ላይ ሊሆን ይችላል። አነስ ያለ ቡና ሻይ አልያም ዉሃ መቀማመሻ አነስ ያለ ሻይ ቤት ይገኛል። ህጻናት የሚጫወቱነት ስፍራም አለ።
እ.አ 1993 አ.ም በሰሜናዊ ጀርመን በምትገኘዉ በፍሌንስቡርግ ከተማ ህጻናት እንደልባቸዉ ከተፈጥሮ ጋር እንዲገናኙ እና ተፈጥሮን እንዲያጣጥሙ በሚል ዘርዘር ባለ በአንድ ጫካ ዉስጥ አንድ የህጻናት መዋያ ከተቋቋመ ወዲህ በተለያዩ የጀርመን ክፍለ ግዛቶች በርካታ የህጫናት መዋያ እና የመጫወቻ ስፍራዎች በደን ዉስጥ ማለት በጫካ ዉስጥ ተቋቁሞአል። በርግጥ በጀርመን ሚገኘዉ ጫካ በአገራችን በአብእዛኛዉ እንደሚታየዉ ወፍ ዘራሽ ሳይሆን የዛፉ አበቃቀል በተፈለገዉ ርቀት የተተከለ፣ ጥቅጥቅ ያለ ደንም ቢሆን የእግረኛ እና የብስክሌእት መንጃ መንገድ ያለዉ ከዛ ባለፈ ከላይ እንደጠቀሰዉ አረፍ የሚባልበት ወንበር የሚገኘት መጸዳጃ ቦታዉ የሚገኝበት ዝናብም ድንገት ቢመጣ እንኳ መጠለያ ከቆርቆር ብጤ የተሰራ ጎጆ ቤት የማይጠፋዉ ነዉ። ታድያ በአሁኑ ወቅት በጀርመን ዉስጥ በግል ፈቃድ ጫካ ዉስጥ የተቋቋመ አንድ ሽ አራት መቶ ያህል ህጻናት መዋያ መኖሩ ተመልኮአል። እዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት ከተቋቋመ አስራ አምስት አመት የሆነዉ ስፕሮክ ሆፍል ህጻናት መዋያ
«ህጻናት መዋያዉ የደን ሃብት ጥበቃ አመት ለተሰኘዉ ለዚህ አመት መለያ ነዉ። ደን ማለት ጫካዉ ለህጻናት ያስፈልጋል? አዎ ለመንጠልጠል ለመጫወት ለመዉደቅ ለመነሳት። ለአዋቂዎች ምን ይጠቅማል? ንጹህ አየርን ለመተንፈስ ከጓደኛ ጋር ሽርሽር ለመዉጣት ለወያየት»
ሃያ ህጻናት በሚዉሉበት የህጻናት መዋያ ዉስጥ ህጻናቱን የምትጠብቀዉ ጀርመናዊት ጋብርኤለ ሮሚሽ ለህጻናቱ በደን ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ እጸዋትን በማሳየት እና በመዳሰስ ስማቸዉን በመንገር የተለያዩ የቀለም ስያሜዎችን መጥርያ በማስተማር ህጻናቱ ከመጀመርያ ጀምሮ ከተፈጥሮ ጋር እንዲወዳጁ ማድረጉ ለህጻናቱ ፈጣን እድገት ጥቃሚ መሆኑን ይገልጻሉ። ህጻናቱ እንደ ሳማ አይነት ቅጠል እንደሚለበልባቸዉ ስለሚያዉቁ አይነኩም፣ በሌላ በኩል ምናልባት በመንገድ ላይ ቀንድ አዉጣ አልያም ሌላ አይነት ነፍሳት ሲያገኙ መርገጥ እንደሌለባቸዉም ያዉቃሉ። በዚህም የሌላን ህይወት መጠበቅም እንዳለባቸዉ ይረዳሉ ሲሉ ይገልጻሉ። የደን ሃብታችን አንዱ የባህላችን መግለጫ ቦታ በመሆኑ ያለንበት የአዉሮጳዉያኑ አመት አለም አቀፉ የደን ሃብት ጥበቃ አመት ተብሎ መሰየሙ ሰሞኑን የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች ሳይዘግቡበት አላለፉም።

No Flash Das German Woman Jazz Orchestra
ምስል DW
Leipziger Buchmesse 2011
የላፕዚጉ አለም አቀፍ የመጽሃፍ አዉደ ርእይምስል Leipziger Messe GmbH/Norman Rembarz

ሰባት ሳምንት ግድም የሆነዉ የሰሜን አፍሪቃዉ የለዉጥ አብዮት ከፖለቲካ ባሻገር የባህል መድረኩንም ሳይዳስስ አልቀረም። በግብጽ የፕሪዝደንት ሙባረክ የሰላሳ አመት በላይ የስልጣን መንበርን ገፍትሮ ከጣለዉ የዉጥ እንቅስቃሴ በኳላ በግብጽ በተለይ በመዲናዋ ይታይ የነበረዉ ባህላዊ እንቅስቃሴ በሩ ተዘገቶ ሰንብቶአል። በተለይ ከሳምንታት ወዲህ በለዉጥ አራማጁ በወጣቱ አኳያም ከለዉጡ ባሻገር የነበረዉ የሙዚቃ የትያትር መድረክ ዳግም ለታዳምያን በሩን መክፈት ጀምረዋል። ካይሮም በየአመቱ የምታካሂደዉን የጃዝ ሙዚቃ ድግስ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በደማቅ ማካሄድዋ ተነግሮላታል። የአንድ ሙዚቀኛ ዋና ፍላጎቱ ሙዚቃ መጫወት እና በቀጣይ እዉቀቱን በትምህርት ማዳበር ነዉ ስትል የምትገልጸዉ ጀርመናዊትዋ የኮለኝ ከተማ የሴቶች የጃዝ ሙዚቃ ቡድን አባል እና የሳክስፎን ሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች ሙዚቃ ለስዋ ህይወትዋ እንደሆን ትገልጻለች። አስራ ሁለት ሴቶችን በሚያካትተዉ የኮለን ከተማዉ የጀርመን የሴቶች የጃስ ሙዚቃ ቡድን አባልም ናት። የጀርመን የሴቶች የጃዝ ሙዚቃ ቡድን አባላት ባለፈዉ ሳምንት በግብጽ በአሌክሳንድርያ ታላቅ የሙዚቃ ድግስን ካቀረቡ በኳላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በካይሮ የጃዝ ድግሳቸዉ ተወዳጅ ያደረጋቸዉን የሙዚቃ ድግስ አቅርበዋል። ከጥር አስራ ሰባት ጀምሮ ተዳፍኖ የነበረዉ የግብጽ ባህላዊ እንቅስቃሴ ከለፈዉ ሳምንት ከሃሙስ ጀምሮ በካይሮዉ በጃዝ የሙዚቃ ድግስ መድረኩን በመነቅነቅ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ጥሩ ስሜትን በግብጻዉያን ላይ አስፍሮአል። በሳምንቱ መጨረሻ ከጃዝ ሙዚቃዉ ትይዩ የግብጽ ህዝብ የህገ-መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ ድምጽ ሲሰጥ ነዉ የዋለዉ። ከዘመናት በዓላ በግብጽ ለመጀመርያ ግዜ ነጻ የሆነ የድምጽ አሰጣት ስነ-ስርአትም እንደነበር ተነግሮአል።
በዘንድሮ በነበረዉ በካይሮዉ የጃዝ የሙዚቃ ድግስ ከሶስት ሽህ በላይ የመግብያ ትኬት መሸጡም ተገልጾአል። በዚህም ከምንግዜዉም በላይ በርካታ ተመልካች እንደነበረ እና የተለያየ እድሜ ያላቸዉ የማህበረሰቡ አባላትም መገኘታቸዉ ተመልክቶአል። በካይሮዉ የጃዝ ፊስቲቫል ላይ የሙዚቃ መድረክ ብቻ ስይሆን ግብጻዉያን የጃዝ ሙዞቃ አፍቃሪዎችም ትምህርታዊ ገለጻን እና ዉይይት አድረዋል።

በግብጽ ፖለቲካና የባህል መድረክ እስከ አለፈዉ ጥር አስራ ሰባት ድረስ ገጥመዉ እንደማያዉቁ የምትናገረዉ ግብጻዊትዋ ሙዚቀኛ ህዝብ የለዉጥ እንቅስቃሴን የመፍራቱን ያህል ከአብዮቱ በኳላ የግብጽ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በግልጽ ሃሳቡን ያለፍርሃት የሚገልጽበት በሁሉ ቦታ ፖለቲካን የማዉራት ነጻነትን ያገኘበት ግዜ ነዉ። በጃዙ የሙዚቃ ድግስ ላይም የተለያ ሁኔታ አልነበረም።
የጀርመን የጃዝ የሙዚቃ ባንድ አባላትም በአሌክሳንድርያ እና በካይሮ ከተሞች የሙዚቃ ድግሳቸዉን ለህዝብ በማቅረብ አዲስ ታሪክን በአስመዘገበችዉ በግብጽ በመገኘታቸዉ እድለኞች እንደሆኑ ይናገራሉ። ጀርመናዊያኑ የጃዝ ሙዚቃ ቡድኖች ቀይ ቀለም ወኔ የሚያላብስ ልበ ሙሉ አብዮታዊንትን ገላጭ በመሆኑን በማሰብ ባለፈዉ አርብ በካይሮ ለህዝብ ድግሳቸዉን ያሳዩበትን መድረክ በቀይ ቀለም በመሸለም እና በቀይ መብራቶችን በመስቀል ነበር የሙዚቃ ድግሳቸዉን ያቀረቡት። እንደ ሙዚቀኞቹ በግብጽ የመጣዉ አብዮት በባህልን በመጠበቁ ረገድ ታላቅ እድገትን እንደሚያመጣ ከሁሉም በላይ በወጣቱ ዘንድ የሚዜሙ ሙዚቃ እና አንዳንድ ስነ-ጥበባዊ ስራ ከዚህ በኳላ በመንግስት አፈናን እንደማይገጥመዉ ያምናሉ። የጃዝ ሙዚቃ እና የግብጽ አብዮት በሚል የባህል መድረክ በሳምንቱ መጨረሻ የካይሮ በጃዝ ሙዚቃ ዘና ብላ መዋላን ዘግቦአል።

Flash-Galerie Elizabeth Taylor gestorben
ምስል dapd

የሆሊዉድዋ የፊልም አክተር ሊዛ ቴለር ትናንት በሰባ ዘጠኝ አመታቸዉ ከዚህ አለም በሞት መለያታቸዉ ሌላዉ የጀርመን የባህል ድረ-ገጾች የዳሰሱት ርዕስ ነበር። የፊልም አክተርዋ የሆሊዉድዋ ኮከብ ሊዛ ቴለር በፊልም ላይ የያዙትን ገጸ-ባህሪ በትክክል በመጫወታቸዉ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን ያተረፉት በፊልም ማዕከሉ በሆሊዉድ እጅግ ዉብ በመሆናቸዉም ነበር። በብሪታንያ ለንደን ዉስጥ በ1932 አ.ም የተወለዱት ሊዛ ቴለር ከሃምሳ በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ በሆኑ ፊልሞች ላይ ዋና ገጸ-ባህሪን ተላብሰዉ ተዉነዋል። ሊዛ ቲለር ቤተሰቦቻቸዉ ከህጻንነት ጀምሮ የፊልም አክተር እንዲሆኑ ይጥሩ ስለነበር ከወጣትነት ግዜ ጀምሮ የህጻናትን ገጸ-ባህሪን በመላበስ ነዉ በፊልሙ መድረክ ላይ መዉጣት የጀመሩት። በዚህም የተነሳ የተለያዩ የፊልም ስራ ድርጅቶች ሊዛ ቴለርን በፊልም ላይ እንዲጫወቱ በርካታ የስራ ኮንትራት በየግዜዉ ያገኙ ነበር፣ ከዚህ ሌላ በግል ህይወታቸዉ ደስተኛ ባለመሆናቸዉ ብቻ ስምንት ግዜ ትዳር ይዘዉ ስምንት ግዜ ፈተዋል። በዚህም በጭንቀት የአልኮል እና የአጽ ሱሰኛ ሆነዉ እንደ ነበር ተመለክቶአል። የሆሊዉድዋ ዉብ ኮከብ የፊልም ተዋናይ ሁለት ግዜ የአኦስካር ሽልማትን አግኝተዋል። ሊዛ ቴለር የኤድስ ቫይረስ በግልጽ በማይነገርበት ዘመን እ.አ 1985 አ.ም የኤድስ ቫይረስን ለመዋጋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመጀመራቸዉም አድናቆትን ተችረዋል። የፊልም ተዋናይዋ የሆሊዉድዋ ንግስት እ.አ 1997 አ.ም መጀመርያ ላይ ጭንቅላታቸዉ ዉስጥ የበቀለን እጢ በኦፕራስዮን ከወጣላቸዉ ወዲህ ትክክለኛ ጤናን አተዉ ከአለም አቀፉ መድረክ መሰወር ጀመሩ። የፖፕ ሙዚቃ ንጉስ ማይክል ጃግሰን ታላቅ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸዉ ሊዛ ቴለር እ.አ 2009 አ.ም ማይክል ጃክሰን በድንገት ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በጤና እክል በሃዘን ስነ-ስርአቱ ላይ ባይገኙም ትክክለኛ ሰዉ አለፈ በማለት የደረሰባቸዉን መራራ ሃዘን መግለጻቸዉ ተነግሮአል። ሊዛ ቴለር በሎስአንጀለስ ማይክል ጃክሰን ህይወቱ ባለፈችበት ሆስፒታል ሶስት በወለዱዋቸዉ እና ሁለት ባሳደጉዋቸዉ ልጆች አጠገብ ህይወታቸዉ ማለፉ ተመልኮአል። በሃምሳዎቹ እና ስድሳዎቹ አመታት በዉበታቸዉ ልብ ስርቅ ያደርጉ የነበሩት ታዋቂዋ ሆሊዉድ የፊልም ተዋናይ ሊዛ ቴለር ስድስት መቶ ቢሊዮን ዶላር ሃብታቸዉን ጥለዉ ነዉ ያለፉት። ገና ግብአተ መሪታቸዉ ሳይፈጸም ታድያ ለመዉረስ የሚደረገዉ ሽኩቻ ተሟሙቆአል።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ