1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ዘመቻ በማግደቡርግ

ረቡዕ፣ መስከረም 3 2010

በጀርመን ከ11 ቀን በኋላ ለሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ  ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመራጭ ድምፅን ለመሳብ ዘመቻቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።  የቀኝ አክራሪው ፓርቲ፣ አማራጭ ለጀርመን፣ አኤፍዴ ትናንት ማታ በምሥራቅ ጀርመኗ የማግደቡርግ ከተማ  የምርጫ ዘመቻ አካሂዶ ነበር።

https://p.dw.com/p/2jtqV
Deutschland AFD Wahlkampfveranstaltung in Magdeburg
ምስል DW/M. Sileshi Siyoum

«ለጀርመናውያን ቅድሚያ መሰጠት አለበት።»አኤፍዴ

በዚሁ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ከተሰሙት ሀሳቦች መካከል የጀርመን ዜጎች ችላ ተብለዋል፣ በጡረታ ላይ የሚገኙ ስድስት ሚልዮን ጀርመኖች ውለታቸው ተረስተው በዝቅተኛ  የኑሮ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፣ እስልምና ሀገሪቱን አስግቷል፣ ሀገሪቱ በስደተኞች ተውጣለች፣ ይህ መቀየር አለበት የሚሉት ይጠቀሳሉ።  ከሌሎች አራት የዶይቸ ቬለ ባልደረቦች ጋር በበርሊን እና በአካባቢዋ በመዘዋወር የምርጫ ዘመቻውን በመቃኘት ላይ ያለው ባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺን  ስለምርጫው ዘመቻ የታዘበውን በስልክ ነግሮኛል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ