1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እሴቶች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 15 2009

ጀርመን ሀገር ውስጥ የሚገኙ 28 ድርጅቶችና ማኅበራት እኛ ማን ነን አንድ ኅ/ሰብ ወይም እንደ ሃገር ምን መሆንስ እንፈልጋለን? ምንስ ላይ ለመድረስ እንፈልጋለን? አንድነታችን የተገነባበት አስኳል ምንድን ነዉ? የቤቱን ጣርያ የሚሸከመዉ ምሶሶ ምን ይመስላል? እንደ ድርና እንደ ማግ ሁላችንም አስተሳስሮ የያዘዉ እሴትስ ምንድን ነዉ? ሲሉ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/2dSCB
Bild am Sonntag Innenminister Thomas de Maiziere
ምስል Bild/Foto: DW/M. Fürstenau

ጀርመን እሴቶችዋ

 ይኸው ጥያቄ በወቅቱ የጀርመን ማኅበረሰብን እያነጋገረ ይገኛል። ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት አሜሪካዉያን በፊናቸዉ የተለያዩ መጻሕፍት ጽፈዋል። እንጊሊዝና ፈረንሳይም ይህንኑ አድርገዋል። በጀርመን ሃገርም ይህንን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት ብዙ መጽሐፍት ታትመዋል። የጀርመን የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቶማስ ዴሚዜር ከሁለት ሳምንት በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ አንስተዉ በአንድ ጋዜጣ ላይ ባስቀመጡዋቸው አስር ነጥቦች መልስ ለመስጠት ሞክረዋል። ይህ ደግሞ በሃገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች ክርክርና ዉይይት እንዲከፈት ምክንያት ሆኖዋል። ጀርመን ማን ናት? ጀርመንን አንድ የሚያደርጋት ምንድን ነዉ? የዛሬው ጀርመን አውሮጳ ዝግጅታችን ትኩረት ነው። 


ማትያስ ፎን ሀይን/ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ