1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የጀርመን እና የኢትዮጵያ የንግድ ጉባዔ

Eshete Bekele
ማክሰኞ፣ ግንቦት 22 2009

የኒደርዛክሰን ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችዉ በጀርመንዋ ሃኖቨር ከተማ ሦስተኛዉ የጀርመንዋ እና የኢትዮጵያ የንግድ ጉባዔ ዛሬ ተካሄደ። በቦታው የተገኙት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ሹማምንት “ሀገሪቱ አላት” ያሉትን የመዋዕለ ንዋይ ዕድሎች ለጀርመን ባለወረቶች ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ጥረት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡  

https://p.dw.com/p/2drJi
Deutschland Hannover 3. German-Ethiopian Business Day
ምስል DW/E. Bekele

M M T/ Q&A _3rd German-Ethiopian Business Day - MP3-Stereo


በዚህ ጉባዔ ላይ  የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር መብርሃቱ መለስ፤ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ ፣ሌሎች ሹማምንቶች ኢትዮጵያዉያን እና ጀርመናዉያን የንግድ ባለሞያዎች እና መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እንዲሁም በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተገኝተዋል። ጎርጎረሳዊዉ 2016 ዓ,ም ኢትዮጵያ 177 ሚሊዮን ይሮ የሚያወጣ ሸቀጥን ለጀርመን ሸጣለች። ይህም ከ 2015 ዓም ጋር ሲነጻፀር በሁለት በመቶ ይበልጣል። ጀርመን ደግሞ በ2016 ማሽኖችንና የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ  350 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ያላቸዉ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ልካለች። ጀርመን ወደ ኢትዮጵያ ያስገባችው የንግድ ሸቀጥ በ 44 በመቶ ጨምሯል ። የሃኖቨሩ የጀርመን ኢትዮጵያ የንግድ ጉባዔ ዓላማ የኢትዮጵያ መንግሥት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እድሎችን ለጀርመን ባለሃብቶች እና ለጀርመን ኩባንያዎች ማስተዋወቅ ነዉ ተብሎአል፤ የጉባኤውን ሂደት የተከታተለው የዶይቼ ቬለ ጋዜጠኛ እሸቴ በቀለ በስልክ ጠይቀነዉ ነበር። 

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሠ