የጀርመን እና የእሥራኤል መንግሥታት ምክክር17 የካቲት 2006ሰኞ፣ የካቲት 17 2006የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በርካታ ሚንስትሮቻቸውን ይዘው ከእሥራኤል መንግሥት ጋ ለመመካከር ዛሬ ወደ ቴል አቪቭ ተጓዙ። የሁለቱ መንግሥታት ካቢኔዎች ነገ በጋራ ከሚያካሂዱት ምክክር በኋላ በጠቅላላhttps://p.dw.com/p/1BEXAምስል dapdማስታወቂያ 19 የትብብር ስምምነቶች እንደሚፈረሙ ይጠበቃል። የሁለቱ ሀገራት ሚንስትሮች ከሚመክሩባቸው ዓበይት ጉዳዮች መካከል የእሥራኤል የሰፈራ መርሀግብር እና አከራካሪው የኢራን አቶም መርሀግብር ይጠቀሳሉ። ቤቲና ማርክስ/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ