1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዉህደት አከባበር

Azeb Tadesseእሑድ፣ መስከረም 24 2002

ጀርመን ብሔራዊ የአንድነት ቀንዋን ለሃያኛ ግዜ አክብራ ዉላለች። እ.አ 1990 አ.ም ጀምሮ ይህ የብሄራዊ አንድነት ቀን በተለዩ የአገሪቷ ግዛቶች ሲከበር የዘንድሮ ብሄራዊ ቀን የፈረንሳይ አዋሳኝ የሆነችዋ የዛርላንድ ግዛት ዛርብሩክን ከተማ ነበር ያስተናገደችዉ።

https://p.dw.com/p/JxTP
የዉህደቱ በአል አከባበር በበርሊንምስል AP

የዛሪ ሃያ አመት በምስራቅ ጀርመን የነበረዉን ስርአት በመቃወም የጀርመንን አንድነት በመፈለግ በተለይ የቀድሞዋ የምስራቅ ጀርመን ሁለተኛ ከተማ ሆና ትታወቅ በነበረዉ በላይፕዚግ ከተማ ነበረዉ ሰላማዊ አመጽ ነበር ለዉህደቱ ታላቅ ሚናን የተጫወተዉ ምንም እንኳ በዝያን ዘመን በቀድሞዋ የሶሻሊስትዋ ምስራቅ ጀርመን እንዲህ አይነቱ ህዝባዊ አመጽ ይሞከራል ይሆናል ብሎ የገመተ ባይኖርም በዛሪዉ ዝግጅታችን ሰላማዊዉ የሻማ መብራት ትግል የጦር መሳርያን የረታበት ስለ ላይፕዚጉን ሰላማዊ አመጽ እንዲሁም ዘንድሮ በበርሊና በዛርብሩከን ስለ ተካሄደዉ በአል በጥቂቱ እንቃኛለን።
የዛሪ ሃያ አመት በቀድሞዋ ሶሻሊስት ምስራቅ ጀርመን በላይፕዚግ ከተማ የተካሄደዉን አይነት አመጽ በነበረዉ ስርአት ይታሰባል ብሎ የገመተ አልነበረም። ተፈርቶ የነበረዉ ደም መፍሰስ ቀርቶ የነበረዉ የኮሚኒዝም ስርአት በሰላም በመፈረካከሱና በመዉደቁም ብዙዎችን አስገርሞአል። ጀርመንን ለሁለት የከፈላት የድንጋይ እና የብረት ግንብ ከመዉደቁ ቀደም ብሎ የምስራቅ ጀርመኑ ሶሻሊስት አንድነት ፓርቲን በመቃወም በተለይ በላይፕዚግ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ ተካሂድዋል። ይኸዉም ጥቅምት ዘጠኝ 70,000ሺ ያህል ህዝብ ሻማ በማብራት አስተዳደሩን በመቃወም ታላቅ ህዝባዊ አመጽ አካሂዶ ነበር። በተለይ የላይብዚጉ የወንጊላዊት ቤተክርስትያን ኒኮላ ኪርሽ ለዚህ አብዮት ታላቅ ሚናን ነበር የተጫወተዉ። በወቅቱ ሰላማዊዉን አመጽ ሲያካሂዱ ከነበሩት መካከል «ነጻ በሆነ አገር ነጻነት ላለዉ ህዝብ» የሚል መፈክር ይዘዉ በላይፕዚጉ አደባባይ እና ኒኮላ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን አካባቢ መስከረም ወር መጀመርያ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመታየታቸዉ በቀድሞዋ የምስራቅ ጀርመን አስተዳደር ወደ እስር የወረዱት ወይዘሮ ሃተን ሃወር
«በዚህ ግዜ ዘብ ጠባቆቹ አካባቢ ጥቅምት 9 ቀን ማለት ነዉ በጣም ዉጥረት እንደነበር ነበር ተመልካቻለሁ። በሌላ በኩል በጣም ከፍተኛ ድምጽ ይሰማ ነበር። ትልልቅ ተሽከርካሪዎችም የሚንቀሰሱ ይመስል ነበር። ብቻ ከፍተኛ ዉጥረት ነበር ይህ ድምጽ ከ 70,000ሺ ህዝብ የመጣ መሆኑ ግን በዝያን ግዜ ለኔ ግልጽ አልነበረም።

Tag der deutschen Einheit Flash-Galerie
አንጌላ ሜርክል በዛርብሩክን ለወዳጆች የፊርማ ማስታወሻ ሲሰጡምስል DPA

ወይዘሮ ሃተን ሃወር ከመጀመርያዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች ተብለዉ እስር ወርደዋል። ህዝቡ በመንገድ እና በአባባይ ቢከለከልም በጸሎት ሰበብ ቤተክርስትያን ቅጽር ግቢ መሰባሰቡን ቀጥሎአል። ቀን በጨመረ ቁጥር ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዉም እየተበራከተ መጣ በቤተክርስትያን ቅጽር ግቢ ብቻ ሳይሆን በአደባባይም ሻማዉን ይዞ ለነጻነቱ ጩኸቱን ማሰማትን ቀጠለ። በሌላ በኩል ህዝቡ መንግስት ምንም አይነት ወታደራዊ ሃይልን ተጠቅም ሰላማዊ ሰልፉን እንዳይበትን «ምንም አይነት ጉልበት እንዳትጠቀሙ» ሲል ጩኸቱን ሲያስተጋባ ስለነበር ፖሊስ ሃይልን ተጠቅሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለመበተንም ጥረት አላደረገም። ቤተክርስትያን ቅይር ግቢ ሻማ ይዞ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣዉ ህዝብ የጦር መሳርያ ይዞ ሰልፉን ለመበተን የቀረበዉህ ፖሊስ የሰላማዊ ጥሪ መልክት የያዘዘዉ የሻማ መብራት ድል አደረገ። ለአማኞች የቆመዉ ቤተክርስትያን በ 1980 ዎቹ ጀምሮ በአገሪቷ ሰላምን ለማምጣት ፍትህን ለማስፈን ለሚደረግ ጥረት መሰባሰብያም ሆነ በዝያን ግዜ ጀርመናዊዉ ራይነር ሙለር አንዱ ነበሩ
«የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ነን፣ ቤተስክያንም እኛን የሰላም ጸሎት እንድናደርስ አሰባስባን ነበር። ያ ደግሞ በቀድሞ ምስራቅ ጀርመን በተወለድንበት ቦታ እምነታችን እንዲጠበቅ እናም የሚታየዉ ኢሰብአዊ ሁኔታ እንዲቀየር የጣርንበት፣ ያሳየንበት ሁኔታ ነበር»
እ.አ 1988 መጀመርያ ላይ በምስራቅ በርሊን በሮዛ ሊክሱንቡርግ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለታሰሩ ሰዎች ጸሎት በመባል የተጀመረዉ የአገሪቷ የሰርቶ አደሮች የአመጽ ትግል በላይፕዚግም ቀጠለ። የመንግስት ፖሊስ የማይደርስበት የቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ በነጻነት ህዝብ የሚወያይበት ለፖለቲካ ጉዳይ መሰባሰብያ ሆነ። በዚህም ምክንያት መስራቅ ጀርመኑ ሶሻሊስት አንድነት ፓርቲ የመዘጋጃ ቤት ሃላፊዎችን እንዲሁም የቤተክርስትያኑን አስተዳዳሪዎች እንዳያስሩ ፍርሃት ቀሰቀሰ በዝያን ወቅት ፍሪድሪሽ ማጊሩስ በአስተዳደር ላይ ነበሩ፣ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ወጣቶችን ጥንቃቄ እንዲወስዱ
«እንደኔ አይነቶቹ ሰዎች፣ የኖሩበት ወቅት፣ ማለት በስታሊን ግዜ፣ በአንድ ለሊት ሰዎች የጠፉበት፣ የት እንደደረሱ ያልታወቀበት ሁኔታ ስለነበር፣ ወጣቶች ይህን ሁኔታ ስለማያዉቁት፣ እንዲያዉቁት በግልጽ ማሳሰብ ነበር»ከዚህ የሻማ ማብራት ሰላማዊ ሰልፍ ትይዩ የመስራቅ ጀርመኑን የሶሻሊስት አንድነት ፓርቲ አባልነት እየለቀቁ በስልጣናቸዉ በመጠቀም ወደ ሌላ አገር የሚፈልሱ የባለስልጣናት ቁጥርም መጨመር ጀመረ። የምስራቅ ክልልን መልቀቅ ያልቻለዉ ህዝብ፣ ድንበር ላይ የቆመውን የግንብ አጥር እየዘለለ፣ የሽቦ የኤሌትሪክ እንዲሁም የድማሚት አጥሩን እየሾለከ ወደ ጎረቤት አገር እንዲሁም ወደ ምዕራብ ጀርመን የዘለቀዉ ህዝብ ቁጥር ጥቂት አልነበረም። በዝያን ግዜ ታድያ በምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመን ድንበር ላይ ያለዉን አጥር ለመሻገር ሲሉ ሕይወታቸዉ የጠፋ ጀርመናዉያን ቁጥር እስካሁን በርግጥ አይታወቅም
ከ20 ዓመት በፊት በህጋዊ መንገድ በዝያን ግዜ ለምስራቅ ጀርመን ወዳጅ ወደ ሆነችዋ ወደ ቼኮስሎቫክያ በመሄድ ፕራግ ውስጥ በሚገኘው የጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክ ኤምባሲ፣ ተገን የጠየቁ 4,500 ያህል የምሥራቅ ጀርመን ዜጎች፣ ወደ ምዕራብ ጀርመን እንዲጓዙ በዝያን ግዜ የቼኮዝሎቫኪያ መንግሥት ጋር ተደራድርው፣ ወደ ምዕራብ ጀርመን እንዲገቡ ያበቁት የዝያን ግዜዉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐንስ ዲትሪኽ ጌንሸር፣ የወሰዱት ጠንካራ እርምጃ፣ እንዲሁም ያሳዩት የዲፕሎማሲ ችሎታ፣ የቀዝቃዛው ጦርነት እንዲያከትምና፣ የጀርመን ውህደትም እውን እንዲሆን ሌላዉ ምክንያት ነበር።
በ 1960 ዎቹ መጀመርያ የምስራቅ ጀርመን መሪ የነበሩት ቫልተር ኡልብሪሽት እንደ አዉሮጻዉያኑ በሰኔ ወር 1961 አ.ም በአንድ አለም አቀፍ መግለጫ ላይ «ምስራቅ እና ምእራብ ጀርመንን የሚከፍል ግንብ ለመገንባት ምንም አይነት እቅድ ወይም ሃሳብ የለንም» ብለዉ ባሳወቁበት ከጥቂት ወራት ኻላ በርሊንን የሚከፍላት ግንብ ተገነባ፥ ትናንት ጀርመን ብሄራዊ የዉህደት ቀንዋን ስታከብር ይህ ጀርመንን ለሁለት የከፈለዉ ግንብ ከፈረሰ ከ20 አመት በኻላ በዛርብሩከን ከተማ ዉስጥ ባለዉ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ህዝቦች ሻማ በማብራት በአላማ ጽኑነት፣ በቆራጥነት እንዲሁም በሰላማዊነት ይህንን ከፋፋይ ግንብ በመገርሰስ አላማቸዉን ላሳኩ የአገሪቷ ህዝቦች ጸሎትና ምስጋናን አቅርበዋል። ይህንንም የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በዛርብሩክን በተደረገዉ ስነ-ስርአት ላይ «ውህደቱ ዕውን ሊሆን የቻለው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ቆራጥነት በማሳየታቸው ነው ሲሉ ነበር የገለጹት» በበርሊን በተካሄደዉ ክብረ በአል ላይ የአስራ አምስት ሜትር ቁመት ያለዉ ከእንጨት የተሰራ ሁለት አሻንጉሊት በታሪካዊዉ የብራንድ ቡርግ በር አካባቢ ትርኢትን በመቶ ለሚቆጠሩ ተመልካቾች አቅርበዋል። ይኸዉም በበርሊኑ ግንብ ሰበብ ተጠፋፍተዉ የነበሩ አንዲት ወጣት እና አጎትዋ ገንቡ ፈርሶ ሲገናኙ ነበር ትርኢቱ የሚያሳየዉ።
በአለም የሙዚቃ አፍቃሪዎች እዉቅ የሆኑት ስኮርፒዎንስ ተብለዉ የሚጠሩት የጀርመን የሙዚቃ ቡድኖች እ.አ1989አ.ም መጨረሻ ላይ ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ለጆሮ ያደረሱት wind of Change የተሰኘዉ ሙዚቃ እዉነትም የጀርመንን ዉህደት ብቻ ሳይሆን የቀዝቃዛዉ ጦርነት ማብቅያን በማሳየቱ በወቅቱ በአለም ደረጃ ተወዳጅነትን አግኝቶ በከፍተኛ ቁጥር ለመሸጥ በቅቶአል።

Klaus Meine Sänger der Band Scorpions
የስኮርፒዎን የሙዚቃ ቡድን አቀንቃኝ ጀመናዊዉ ክላዉስ ማይነምስል AP