1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዉህደት እና ኢትዮጽያዉያን

እሑድ፣ መስከረም 30 2003

ጀርመናዉያን ከአራት አስርተ አመታት ክፍፍል በኋላ አንድ ሆነዉ በፍቅር መኖር የጀመሩበትን ሃያኛ ዓመት መታሰቢያ በደማቅ አክብረዋል።

https://p.dw.com/p/Pabn
የበርሊኑ ግንብ በምዕራብ በርሊን አኳያምስል Andrzej Stach


ጀርመንን በምስራቅ እና በምዕራብ ከፍሎ የነበረዉ ርዕዮተ አለም የቀዝቃዛዉ ጦርነት አብቅቶ በርሊንን ለሁለት የከፈለዉ ግንብ ሲገረሰስ ህዝብ ያለምንም ችግር አንድ ሲሆን ያዪ በቀድሞዋ ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ጀርመን ይኖሩ ተማሪዎች ዛሪ ጀርመን የተለያዩ የአለም ህዝቦች የተለያዩ ባህልና ሃይማኖትን ይዘዉ በፍቅር የሚኖሩባት መሆኗን ይመሰክራሉ። የዛሪዉ ቅንብራችን በጀርመን የተለያዩ ድርጅቶች ዉስጥ በሞያቸዉ የሚሰሩ ኢትዮጽያዉያን ስለጀርመን ዉህደት ያዪትን ያሳለፉትን እንዲያጫዉቱን ጋብዘናል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

looking for Freedom ነጻነቴን እሻለሁ ይሰኛል በርሊንን ለሁለት የከፈለዉ ግንብ እንደተገረሰ የተዜማ በመሆኑ የጀርመን ዉህደት መለያ ሙዚቃ መሆኑ ይነገርለታል። በቀድሞዋ ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ጀርመን የህክምና ትምህርት ለመከታተል የትምህርት እድል አግኝተዉ ከመጡ ኢትዮጽያዉያን መካከል በአሁኑ ወቅት በዛክሶኒ አንሃልት ግዛት ዉስጥ በምትገኘዉ ቦርገን ላንድ ክራይስ ከተማ ያለዉ ትልቅ ሆስፒታል ዋና ተጠሪ ሆነዉ የሚያገለግሉት ዶክተር መኮንን በቀለ ነጻ የትምህርት እድል እንደ አዉሮጻዉያኑ አቆጣጠር 1985አ.ም በምስራቅ ጀርመን ላይፕዚግ ከተማ ለመጀመርያ ግዜ የገቡት... ያድምጡ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ