1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ውህደትን የሚዘክረው ታላቁ ሩጫ

ረቡዕ፣ መስከረም 19 2008

በኢትዮጵያም እለቱ አዲስ አበባ ውስጥ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ እንደሚዘከር በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮአሂም ሽሚት እና የታላቁ ሩጫ አዘጋጅ አትሌት ኅይሌ ገብረ ሥላሴ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/1GgCB
Äthiopien Deutsche Botschaft in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

[No title]


የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 22፣ 2008 በጎርጎሮሳዊው ኦክቶበር 3፣ 2015 ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመን ተዋህደው አንድ አገር ከሆኑ 25 ዓመት ይደፍናል። ይህ የውህደት ቀን ጀርመን ኤምባሲዎቿ በሚገኙበት ሃገራት ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በኢትዮጵያም እለቱ አዲስ አበባ ውስጥ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ እንደሚዘከር በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮአሂም ሽሚት እና የታላቁ ሩጫ አዘጋጅ አትሌት ኅይሌ ገብረ ሥላሴ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን አገባ ልኮልናል ።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ