1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሳውዲ ጉብኝት

ሰኞ፣ ጥር 3 2002

የጀርመኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በፋርስ ባሕረ-ሰላጤ አካባቢ አገሮች ሲያካሂዱት የቆየውን የስድሥት ቀናት ጉብኝት ለማጠቃለል ዘሬ ወደ የመን ተሻግረዋል።

https://p.dw.com/p/LR02
ቬስተርቬለ ከንጉስ አብደላሕ ጋርምስል AP

ሰፊ የምጣኔ-ሐብት ዘርፍ ልዑካንን አስከትለው ወደ አካባቢው የተጓዙት ቬስተርቬለ ቀደም ሲል ሳውዲት አረቢያን፣ ካታርንና የተባበሩ አረብ ኤሚሮችን ሲጎበኙ በሶሥቱም አገሮች ያካሄዱት ንግግር የሁለት ወገን የኤኮኖሚ ግንኙነትን ለማጠናከሩ ጉዳይ ዓቢይ ትኩረት የሰጠ ነበር። እርግጥ የመካከለኛው ምሥራቅ ውዝግብ፣ የኢራን አቶምና የአፍጋሃኒስታን ሁኔታ፤ እንዲሁም አል-ቃኢዳ በየመን የደቀነው አደጋም በሰፊው አነጋግሯል። ነቢዩ ሲራክ በቬስተርቬለ የሳውዲት አረቢያ ጉብኝት ላይ የላከው ዘገባ የሚከተለው ነው።

ነቢዩ ሲራክ

መስፍን መኮንን

አርያም ተክሌ