1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ውህደት

ዓርብ፣ የካቲት 11 2003

በኢትዮዽያና በጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ሆኖታል። የተለያዩ የጀርመን የልማትና የትብብር ድርጅቶችም በኢትዮዽያ የተለያዩ አከባቢዎች በመግባት ልማታዊ ስራዎችን ማከናወን ከጀመሩም ሰንበት ብለዋል።

https://p.dw.com/p/R2JX
ምስል picture alliance / dpa

እነዚህ የጀርመን የልማት ድርጅቶች ኢትዮዽያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተናጠል፤ ፕሮግራምና ወጪያቸውም ለየብቻ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አካሄድ የገንዘብ ብክነትንና የፕሮግራሞች መደራረብን በማስከተሉ በአንድ ድርጅት ጥላ ስር እንዲሆኑ ከሰሞኑ ተወስኗል። የጀርመን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ድርጅት ወይም ጂ.አይ.ዜድ በመባል ከዚህ በኋላ በአንድነት የሚጠቃለሉት የጀርመን ድርጅቶች አቅማቸውን አስተባብረው ለተሻለ ስራ እንደተነሱ አዲስ አበባ ያለው የጀርመን ኤምባሲ የሰጠው መግለጪያ ላይ ተገልጿል።

ጌታቸው ተድላ

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ