1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የምርጫ ስርዓት ና ፓርላማው

ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 2001

የጀርመን የህዝብ ዕንደራሴዎች ምክር ቤት በፌደራል ጀርመን የፓለቲካ ስርዓት ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ። የህዝብ ዕንደራሴዎች አጠቃላይ ምርጫ በየአራት ዓመት አንዴ ይካሄዳል ።

https://p.dw.com/p/JFSz
ምስል AP

ዕንደራሴዎች የሚመረጡትም በአጠቃላይ ፣ በቀጥተኛ ፣ በነፃ በዕኩል እና በሚስጥራዊ ምርጫ ነው ። በጀርመን ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ዜጋ ያለአንዳች ተፅዕኖ መምረጥ ይችላል ። በጀርመን አጠቃላይ የምክር ቤት ምርጫ እያንዳንዱ መራጭ ሁለት የምርጫ ድምፅ አለው።

« በኛ ሀገር ህዝቡ በቀጥታ ለዕጩ ተወዳዳሪ አንድ ድምፅ እንዲሁም ለሚፈልገው ፓርቲ ሌላ ድምፅ የሚሰጥበት የምርጫ ስርዓት ነው ያለው ። »

የጀርመን ምክርቤት የህዝብ ግንኙነት ባልደረባ ክላውስ ሂንተርላይትነር

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ