የጀርመን የነጻ ትምህርት እድል
ሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2008ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሃሙስ አዲስ አበባ ዉስጥ በተካሄደዉ ሥነ-ስርዓት ላይ፤ በኢትዮጵያ በባሕርዳር ዩንቨርስቲ እንዲሁም በናሚቢያና ታንዛንያ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች በሚሰጡ የ «ፒ ኤች ዲ» ፕሮግራሞች አንድ መቶ አፍሪቃዉያን ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ ተነግሮአል። በዚህ መድረክ ላይ ተገኝተዉ የነፃ ትምህርት እድሉን ይፋ ያደረጉት የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቶማስ ሲልበርሆርን በሦስቱ ሃገራት ዩንቨርስቲዎች ለዶክትሪት ዲግሪያቸው ለሚማሩ አፍሪቃዉያን የትምህርትና የቀለብ ሙሉ ወጫቸዉን የሚችለዉ የጀርመን መንግሥት እንደሚሆንም አስታውቀዋል። ዝግጅቱ ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር ዘገባዉን ልኮልናል።
ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ