1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የጦር ሠራዊትና የአፍጋኒስታን ተልዕኮው

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2003

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ባለፈው ቅዳሜ ሳይታሰብ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን የሀገራቸውን ወታደሮች ጎበኙ። ጀርመናውያኑ ወታደሮች በጦርነት ላይ እንደሚገኙ ሜርክል በዚሁ ጉብኝታቸው ወቅት ባሰሙት ንግግራቸው በግልጽ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/Qgcv
ምስል dapd

ሜርክል በማዛር ኢ ሻሪፍ ከተማ ከአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት ሀሚድ ካርዛይ እና ከዓለም አቀፍ የአፍጋኒስታን ጸጥታ አስጠባቂ ኃይላት፡ በምህጻሩ አይዛፍ መሪ ጀነራል ዴቪድ ፔትረየስ ጋ ተገናኝተው ሀሳብ ተለዋውጠዋል። ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የአፍጋኒስታን ጉብኝት ጥቂት ቀደም ሲል አንድ የሀያ አንድ ዓመት ጀርመናዊ ወታደር በአደጋ ህይወቱን አጥቷል። ዛቢነ ማታይ እንደዘገበችው፡ በአፍጋኒስታን ተልዕኮ እስከዛሬ ድረስ የሞቱት ጀርመናውያን ወታደሮች ቁጥር አሁን አርባ አምስት ደርሶዋል።

ዛቢነ ማታይ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ