1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት

ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2004

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀርመን አምባሳደር ፔተር ቪቲሽ እንዳሉት መስከረም አጋማሽ ላይ የመንግስታት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የአረቡ አለም ህዝባዊ አብዮት በመካከለኛው ምሥራቅ ባመጣቸው ለውጦችና በአረብ ሊግ ሚና ላይ የሚያተኩር ጉባኤ ይካሄዳል ።

https://p.dw.com/p/1653w
(110318) -- NEW YORK, March 18, 2011 () -- Germany's Ambassador to the UN Peter Wittig speaks after voting on Libyan resolution during an open meeting of the UN Security Council at the UN headquarters in New York, the United States, March 17, 2011. The UN Security Council on Thursday adopted a resolution to authorize a no-fly zone over Libya and called for "all necessary measures," excluding troops on the ground, to protect civilians under threat of attack in the North African country. (/Bai Jie)(zyw)
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመን የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት
ለአንድ ወር የሚዘልቀውን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነት ባለፈው ቅዳሜ የተረከበችው ጀርመን በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍጋኒስታን ላይ ያተኮሩ አብይ ጉባኤዎችን እንደምታዘጋጅ አስታወቀች ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጀርመን አምባሳደር ፔተር ቪቲሽ እንዳሉት መስከረም አጋማሽ ላይ የመንግስታት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚካፈሉበት የአረቡ አለም ህዝባዊ አብዮት በመካከለኛው ምሥራቅ ባመጣቸው ለውጦችና በአረብ ሊግ ሚና ላይ የሚያተኩር ጉባኤ ተጠርቷል ። ከዚያ አስቀድሞ ደግሞ በአፍጋኒስታን ከኔቶ መውጣት በኋላ የሚኖረውን የሥልጣን ሽግግር የተመለከተ ልዩ ውይይት ይካሄዳል ። ሆኖም አምባሳደሩ እንዳሉት የሶሪያ ውዝግብ በአጀንዳ አልተያዘም ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አለው

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ