1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ማራቶን

ዓርብ፣ ሰኔ 25 2002

በትናንትናው ዕለት በዚህ በጀርመን የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሥር ሰዓታት ከፈጀ ማራቶን በኋላ በክርስቲያን ዴሞክራቱ ሕብረት ዕጩ ፖለቲከኛ በክሪስቲያን ዉልፍ አሸናፊነት ለይቶለታል።

https://p.dw.com/p/O8NP
ምስል picture alliance/dpa

ቩልፍ በተቃዋሚዎቹ ሶሻል ዴሞክራቶችና በአረንጓዴው ፓርቲ የሚደገፉትን ዋነኛ ተፎካካሪያቸውን የአሂም ጋውክን አሸንፈው የተመረጡት አሥር ሰዓት ከፈጀ ሶሥት ሙከራ በኋላ ነው። ለዚህም በተለይ ምክንያት የሆነው አንዳንድ የጥምሩ መንግሥት እንደራሴዎች ለራሳቸው ዕጩ ድምጽ በመንፈግ ዉልፍ አስፈላጊውን የብዙሃን ድጋፍ ቀድመው እንዳያረጋግጡ ማድረጋቸው ነበር። ክሪስቲያን ዉልፍ ሶሥት ጊዜ በተካሄደ ድምጽ አሰጣጥ በመጨረሻ ቢመረጡም ታዛቢዎች ከዚህ ቀደም ያልተለመደውን ውጣ ወረድ የተመለከቱት ለቻንስለር አንጌላ ሜርክል ሽንፈት እንደሆነ አድርገው ነው።

ይልማ ሃይለ ሚካኤል

መስፍን መኮንን

አርያም ተክሌ