1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ፕሬዚዳንት የናይጄርያ ጉብኝት

ሰኞ፣ ጥር 30 2008

በርካታ የኤኮኖሚ ጉዳይ ባለሞያዎችን ያስከተሉት የጀርመኑ ርዕሠ ብሔር ዮአሂም ጋዉክ በምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ሀገር ናይጄሪያ ለአራት ቀናት የሚዘልቅ ጉብኝታቸዉን ዛሬ ጀመሩ።

https://p.dw.com/p/1Hrfw
Bundespräsident Abflug Gauck Staatsbesuch Nigeria
ምስል picture-alliance/dpa/W. Kumm


ፕሬዝደንት ጋዉክ በዚህ ጉብኝታቸዉ ከናይጀርያ አቻቸዉ ሙሀማዱ ቡሃሪ ጋር ሽብርተኝነትን መዋጋትን በተመለከተ በሰፊዉ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል። ከዚህም ሌላ ጉብኝታቸዉ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉን የኤኮኖሚ እና ሌሎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነም ተጠቁሟል። ፕሬዝደንቱ ከናይጀሪያ ጉብኝታቸዉ በኋላም የፊታችን ዓርብ ማሊን ለጥቂት ሰዓታት እንደሚጎበኙም ተገልፆአል። ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደባት ናይጀሪያ ነፃ የመገናኛ ብዙሃን እንዳሏት ይነገርላታል። ናይጀሪያ ከአፍሪቃ በነዳጅ ዘይት ኃብቷ ብትታወቅም በአንፃሩ በሀገሪቱ የሙስናና ድሕነት ይዞታዉ ከፍተኛ እንደሆነም ይወራል። ቦኮ ሀራም የሚያደርሰዉ የሽብር ጥቃት እና እገታም ምዕራብ አፍሪቃዊቱን ሀገር የሚያሳስብ ጉዳይ ነዉ። የበርኒኑ ወኪላችን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ