1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል ልዩ ዘገባ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2006

የገና በዓልን በማስመልከት ከአዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ልዩ የበዓል ዘገባዎች ደርሰውናል። ፍራንክፉርት እና ለንደን የሚገኙ ወኪሎቻችንም በየከተሞቹ የተካሄዱ የበዓል መሰናዶዎችን ተከታትለው ያጠናቀሩትን ልከውልናል።

https://p.dw.com/p/1Amex
ምስል Alexander Hoffmann/Fotolia

የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ መቅረፀ-ድምፁን ይዞ በመዲናይቱ የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር፣ ወደየ አብያተክርስቲያናቱ የሚያቀኑ ምዕመናንን እና በመንገድ ላይ ያገኛቸውን የተወሰኑ ሰዎች አነጋግሯል። መስቀል አደባባይ በተዘረጋው የበዓል አውደርዕይ እና ትርዒትም ላይ ተሳታፊ ነበር፤ ዘገባ አለው።

የገና በዓል ከኢትዮጵያ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድም በልዩ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ በላከው ዘገባ በዓሉ አሜሪካን ውስጥ እጅግ በደመቀ ሐይማኖታዊ ስርዓት እየተከበረ መሆኑን ገልጾልናል። አበበ በዓሉን ከዋዜማው አንስቶ ተከታትሎታል።

እዚህ ጀርመን ሀገርም ፍራንክፈርት ከተማ ውስጥ የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል በልዩ ድምቀት ነው የተከበረው። በዓሉን ኢትዮጵያውያን ከኤርትራውያን ወንድሞቻቸው ጋር በአንድነት ነው ያከበሩት። ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን ትናንት ምሽት ፍራንክፈርት ከተማ ወደ ሚገኘው የመድሀኔዓለም ቤተክርስትያን አቅንቶ ነበር።

ከጀርመን ተነስተን በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ሚኖሩባት የብሪታንያ መዲና ለንደን ነው የምናቀናው። በለንደን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን ክርስትያን ምዕመናን በዓለ ልደቱን ከዋዜማው አንስቶ ሲያከብሩ ነው የዋሉት። የለንደኗ ወኪላችን ሀና ደምሴ ለንደን በሚገኙ ሁለት አብያተክርስትያናት በመገኘት ዘገባ አጠናቅራለች።

ወኪሎች

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ