1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል በአዕምሮ እድገት ዝግመት እንክብካቤ ማዕከል

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2008

በዩናይትድ ስቴትስ ይኖሩ የነበሩት ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ስለአዕምሮ እድገት ዝግመት የሚያውቁት አንዳች ነገር አልነበረም። ወ/ሮዋ በእርግጠኝነት በወቅቱ አንድ ነገር ግን ያውቁ ነበር።

https://p.dw.com/p/1HZwO
Äthiopien Weihnachtsfest in Addis Abeba
ምስል DW/G.T. Hailegiorgis

[No title]

የአራት አመት ልጃቸው ጆጆ ከሌሎች ሁሉ የተለየ መሆኑን።በጎርጎሮሳዊው1995 ዓ.ም.በአንድ ቴሌቭዥን ስለ የአዕምሮ እድገት ዝግመት የተዘጋጀ መሰናዶ ከተመለከቱ በኋላ ግን የልጃቸውን ነገር ጠረጠሩ። ከብዙ አመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ወ/ሮ ዘሚ ለልጃቸው አስፈላጊውን ድጋፍና ክብካቤ እንዲያገኝ ማድረግ ቢችሉም በአገሪቱ ያለውን ችግር ሲታዘቡ ማዘናቸው አልቀረም። ኢትዮጵያ እና መሰል ደሐ አገሮች የአዕምሮ እድገት ዝግመት ላይ በቂ የህክምና ማዕከላት የሉም። ወ/ሮ ዘሚ በኢትዮጵያ የኒያ ፋውንዴሽን አዕምሮ እድገት ዝግመት እንክብካቤ ማዕከልን መስርተዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ወደ ማዕከሉ ጎራ ብሎ የገና በዓል አከባበርን ቃኝቷል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ