1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል እና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2008

ኢትዮጵያ የእየሱስ ክርስቶስ በዓልን ለ2008ኛ ጊዜ አክብራለች። ቅዱስ ላሊበላ እና እየሱስ ክርስቶስ የተወለዱበት ዕለት ተመሳሳይ በመሆኑ በአንድ ቀን በድምቀት እንደሚከበር ዶ/ር አባ ሐይለማርያም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/1Ha0h
Lalibela - Orthodoxe Christen
ምስል Reuters/Goran Tomasevic

የገና በዓል እና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት

የገና በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ የጁልየስ የዘመን ቀመርን በሚከተሉ በመላው ዓለም የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ተከብሮ ዉሏል። የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ዘንድሮ ሲከበር ለ2008ኛ ጊዜ ነው። በዓሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ በቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዓርብ፤ ታኅሣሥ 29 ቀን፣ በድምቀት እንደሚከበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክህነት ምክትል አስተዳዳሪ ዶ/ር አባ ኃይለማሪያም መለስ አስረድተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ