1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገንዘብ ማጭበርበር ቅሌት

ሰኞ፣ መጋቢት 26 2008

በጣም ብዙ የሀገር መሪዎች፣ ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ ፖለቲከኞች፣ ግብር እንዳይከፍሉ ሲሉ ገንዘባቸውን ወደ ፓናማ በድብቅ ማሸሸታቸው ተጋለጠ። ስማቸው ከዚሁ ቅሌት ጋር ተያይዞ የተጠቀሱት ታዋቂ ሰዎች ገንዘባቸውን መንበሩን ፓናማ ባደረገው «ሞሳክ ፎኔስካ» በተባለ ድርጅት ስር በከፈቱት የሽፋን አድራሻ ማስቀመጣቸው ነው የተሰማው።

https://p.dw.com/p/1IP98
Deutschland Titelseite Süddeutsche Zeitung Panama Papers
ምስል DW/B. Kling

[No title]

ገንዘባቸውን በድብቅ አሸሽተው በፓናማ አስቀምጠዋል ከተባሉት መካከል በስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች የታወቁ ግለሰቦች እና ሕገ ወጥ የእፅ ነጋዴዎችም ይገኙባቸዋል። ይህንን ያጋለጠው ከአንድ መቶ በላይ ከሆኑ ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር የአንድ ዓመት ምርመራ ያካሄደው የጀርመናውያኑ ዕለታዊ «ዚውድዶይቸ» ጋዜጣ ነው።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ