1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገንዘብ ርዳታ ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት

ሰኞ፣ ጥቅምት 17 2007

የአውሮጳ ህብረት፣ የዓለም ባንክ እና ሌሎች ያካባባ የልማት ባንኮች ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ስምንት ቢልዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገቡ። ይህ ዜና ይፋ የሆነው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ከዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ኪም ጋር ዛሬ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ ነው።

https://p.dw.com/p/1DcwY
Logo Zentrale IWF in Washington
ምስል DW/A.Becker

ዋና ጸሐፊው እንዳስታወቁት፣ ገንዘቡ በኤኮኖሚያዊው ዘርፍ እና በፖለቲካው መረጋጋት ብዙም ያልተነገረለትን ጉልህ መሻሻል ያሳየው የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ድህነትን ለመታገል እና ዘላቂ ዕድገት ለማስገኘት ለጀመረው ጥረቱ መደገፊያ ይውላል። የዓለም ባንክ 1,8 ቢልዮን ፣ የአውሮጳ ህብረት 3,7 ቢልዮን፣ የአፍሪቃ የልማት ባንክ 1,8 ቢልዮን ዶላር፣ እንዲሁም፣ የሙሥሊምሞች የልማት ባንክ 1,8 ቢልዮን ዶላር በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት እንደሚሰጡ ነው ያመለከቱት። ገንዘቡ የሚሰጣቸው ሀገራት ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳን እና ዩጋንዳ ናቸው።

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ