1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋምቢያ የሠብአዊ መብት ይዞታ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 2004

እንዳዴ እንደ አርቆ አሳቢ መሪ ጋምቢያን በነዳጅ ዘይት-አበሸብሻታለሁ፥ ይላሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ቅጠል በጣሽ-ወይም ሥር ማሽ HIV-AIDSን ፈዋሽ ነኝ ይላሉ።ጃማሕ። ሕዝባቸዉን ግን እንደ ወታደራዊ አምባገነን ሰጥለጥ አድርገዉ መግዛታቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/15e7T
FILE - In this June 30, 2011 file photo, Gambian President Yahya Jammeh stands outside the Sipopo Conference Center in Malabo, Equatorial Guinea, ahead of the opening session of the 17th African Union Summit. A movement to coronate President Jammeh as King of Gambia may have lost steam, but this ruler of 17 years who claims he can cure AIDS and infertility is all but certain to remain in power after a Thursday, Nov. 24, 2011 presidential vote. (Foto:Rebecca Blackwell, file/AP/dapd).
ፕሬዝዳንት ያሕያ ጃማሕምስል AP

የጋምቢያ መንግሥት በተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥ በነፃ ጋዜጠኞችና በመብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈፅመዉን በደል እንዲያቆም የመብት ተሟጋቾች ጠየቁ።ባለፈዉ ዕሁድ «የጋምቢያ ቀን የተሰኘዉን» አመታዊ ዕለት በአደባባይ ሠልፍና ስብሰባ ያከበሩት ወገኖች እንደሚሉት የጋምቢያ መንግሥት የሚፈፅመዉ የመብት ረገጣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ።ተሟጋቾቹ የፕሬዝዳት ያሕያ ጃማሕ መንግሥት ሠብአዊ መብት እንዲያከብር የአፍሪቃ ሕብረት፥ የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብና አለም አቀፉ ማሕበረሰብ ተፅዕኖ ማሳረፍ አለባቸዉ ባዮች ናቸዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።

መቶ አለቃ ያሕያ ጃማሕ-እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1994 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ደቡብ-ምሥራቅ ሴኔጋል ጠረፍ የተሰነቀረችዉን ትንሽ ሐገር በትልቅ ጡንጫቸዉ ፈጥርቀዉ እያንደያዟት ነዉ።እንዳዴ እንደ አርቆ አሳቢ መሪ ጋምቢያን በነዳጅ ዘይት-አበሸብሻታለሁ፥ ይላሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ቅጠል በጣሽ-ወይም ሥር ማሽ HIV-AIDSን ፈዋሽ ነኝ ይላሉ።ጃማሕ። ሕዝባቸዉን ግን እንደ ወታደራዊ አምባገነን ሰጥለጥ አድርገዉ መግዛታቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

ጃማሕ፥ ጋምቢያ ከብሪታን ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ የመሯትን ፕሬዝዳት ዳዉዳ ካይራካባ ጃዋራን ከሥልጣን ያስወገዱበትን የጎርጎሮሳዉያኑን ሐምሌ ሐያ-ሁለትን የጋምብያ «ትክክለኛ የነፃነት ቀን» ብለዉ-በየአማቱ ያስከብሩታል።ለጋምብያ ሕዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገሉ ወገኖች ግን ዕለቱን የፕሬዝዳት ጃማሕ አገዛዝ የሚፈመዉን ግፍ ለማጋለጥ ይጠቀሙበታል።

ዘንድሮ፥- ባለፈዉ ዕሁድ አራተኛ አመታቸዉ።
                
«በየዓመቱ ሐምሌ ሃያ-ሁለት ጋምቢያ ዉስጥ ያለዉን የሠብአዊ መብት ጥሰት እናስታዉሳለን። ፕሬዝዳት ጃማሕ የሠብአዊ መብት ጥበቃን እንዳሾፉበት ነዉ።ጋምቢያ ዉስጥ ያለዉ የመብት ጥሰት ሲታይ ይሕ ዕለት እራሱ የነፃነት ቀን መባሉ አስቂኝ ነዉ።»

ይላሉ የጋቢያ ጉዳይ አጥኚዋ ሊዛ ሼርማን።

ዘንድሮ በየሐገሩ አደባባይ የወጡት የመብት ተሟጋቾችና የጋምቢያ ወዳጆች የታሠሩ  ጋምቢያዉያንን ምሥል አንግበዉ፥ በየደረታቸዉ «ነፃነት ለጋምቢያ» የሚል መፍክር ለጥፈዉ፥  ዓለም በፕሬዝዳት ጃማሕ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የጋምቢያ መንግሥት በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና ነፃ ጋዜጠኞችን ማሰር-ማሰደዱን የመብት ተሟጋቾቹ አስታዉቀዋል።ዘንድሮ በግንባር ቀደምትነት ያነሱት ግን የታሰሩትን ዶክተር ጃኔ የተሰኙትን ተቃዋሚ ፖለቲከኛን ጉዳይ ነዉ።

ሊዛ ሼርማን እንደሚሉት ሠልፈኞቹ ከጋምቢያና የምዕራብ አፍሪቃን የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ኤኮዋስን) ተዘዋዋሪ የፕሬዝዳትነት ሥልጣን ከያዘችዉ ከኮትዲቯር ኤምባሲ ፊት ለፊት ተኮልኩለዉም ነበር።
                   
«በዚሕ እንቅስቃሴያችን የተለያዩ ወገኖች አሉበት፥ የመብት ተሟጋቾች እና በመላዉ ዓለም ለተቃዉሞ አደባባይ የሚወጡ፥ ከጋሚቢያና ከኮትዲቯር ኤምባሲ ፊትለፊት የሚሠለፉ ሰዎች አሉ።-የኮትዲቯሩ ፕሬዝዳት የኤኮዋስ መሪም በመሆናቸዉ ሥለ ጋምቢያ የሠብአዊ ይዞታ የሆነ ነገር እንዲያደርጉ ለማሳሰብ።»

ባለፉት አራት ዓመታት ያደረጉት ትግል በተለይ ከኢኮዋስና ከአፍሪቃ ሕብረት አበረታች ድጋፍ ማግኘቱን ሼርማን ይነጋራሉ።የኢኮዋስ ፍርድ ቤት የጋምቢያ መንግሥት አላግባብ ላሳራቸዉ አንድ ግለሰብ መቶ ሺሕ ዶላር፥ ላስገረፋቸዉ ለሌላ ሰዉ ደግሞ ሁለት መቶ ሺሕ ዶላር ካሳ እንዲከፍል ፈርዶበታል።የአፍሪቃ ሕብረትም የጋምቢያ መንግሥት የሠብአዊ መብት ይዞታዉን እንዲያሻሽል አስጠንቅቋል።

ቅጣት ማስጠንቀቂያዉ ግን ሼርማን እንደሚሉት የፕሬዝዳት ጃማሕ መንግሥት የሚፈፅመዉን ግፍ አላስለወጠም። እንደገና ሼርማን
         
«እኛ ያገኘነዉ፥-የጋምቢያ የሠብአዊ መብት ሁኔታ በጣም አስከፊ ሆኖ መቀጠሉን ነዉ።የመንግሥት ተቃዋሚዎች፥ ጋዜጠኞች፥ የመብት ተሟጋቾችና ሌሎችም ሰዎች በየጊዜዉ ይዋከባሉ፥ ይታሠራሉ፥ ሥራቸዉን እንዳይሰሩ ግፊት ይደረግባቸዋልም።»

አስራ-አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ስኩዬር ኪሎ ሜትር-ትሰፋለች።የሕዝቧ ብዛት አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ነዉ።ከደሴቶች በስተቀር ከአፍሪቃ ሐገራት ሁሉ ትንሿ ናት።ጋምቢያ።

Supporters of President Yaya Jammeh gather on the beach in front of his residence to celebrate his reelection, in Banjul, Gambia Saturday, Sept. 23, 2006. Thousands of people turned out to celebrate Jammeh's election to a third term. (AP Photo/Rebecca Blackwell)
ምስል AP
An election worker displays marbles cast for President Yaya Jammeh at one polling station to political party representatives during vote counting in Banjul, Gambia Friday, Sept. 22, 2006. Gambians voted for president Friday, dropping a marble into a bin marked with their candidate's color, in elections that longtime President Yaya Jammeh is widely expected to win. (ddp images/AP Photo/Rebecca Blackwell) bpk / Gerhard Kiesling
ምስል AP

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ






        

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ