1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዛ ጦርነትና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ሠላም

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2001

አመቱ ዞሮ ሲገጥም፥ የመሰለዉን እንደመሰለ የማስቀረቱ አዚም አነጋግሮ ሳያበቃ፣ ጋዛ ትጋይ ገባች።

https://p.dw.com/p/GSQs
ስሜን ጋዛምስል AP

አምና ይሕን ጊዜ የአለም ዘዋሪዎች የዲፕሎማሲያ ዘመቻቸዉን በጎ ዉጤት-ድምቀት፤ የግብዣ ጉባኤቸዉን ድንቅ ሥምረት፣ የእቅዳቸዉን ጥራት-ፅዳት፣ የቃል-ምሕላቸዉን ፅናት ሲያንቆረቁሩት ለዚያ ምድር ሰላም እስከዚያ ዘመን ድረስ የተሞከረ-የተለፋዉን ሁሉ የሚያስረሳ መስሎ ነበር። ማስመሰልን-እንጂ ማሆንን አያዉቅም።መካከለኛዉ ምሥራቅ።አመቱ ዞሮ ሲገጥም፥ የመሰለዉን እንደመሰለ የማስቀረቱ አዚም አነጋግሮ ሳያበቃ፣ ጋዛ ትጋይ ገባች።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የጋዛን ዉጊያ እስታከን እንደገና እስራኤል-ፍልስጤም እንላለን አብራችሁኝ ቆዩ።