1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኛ ተመስገን ምሥክሮች ጉዳይ በፍርድ ቤት

ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2005

ርድ ቤቱ ፤ የጋዜጠኛ ተመሥገን ምሥክሮች የሆኑት ፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማርያምና ዶ/ር ያሬድ ለገሠ ለምሥክርነት ሊቀርቡ አይገባም በማለት ያመለከተውን ነው ውድቅ በማድረግ እንዲመሠክሩ የፈቀደው።

https://p.dw.com/p/18hWB
ምስል DW

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ አሥራ ስድስተኛ ወንጀል ችሎት፤ ልደታ ምድብ፣በጋዜጠኛ ተመሥገን ደሳለኝ ላይ ክስ የመሠረተው ዐቃቤ -ህግ ፣ የመከላከያ ምሥክሮችን ቃል እንዳይሰማ ቢቃወምም፣ ፍርድ ቤቱ የሚከለክልቸው ህግ የለም በማለት መወሰኑ ተነግሯል። ፍርድ ቤቱ ፤ የጋዜጠኛ ተመሥገን ምሥክሮች የሆኑት ፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማርያምና ዶ/ር ያሬድ ለገሠ ለምሥክርነት ሊቀርቡ አይገባም በማለት ያመለከተውን ነው ውድቅ በማድረግ እንዲመሠክሩ የፈቀደው። ምሥክር የማዳመጡ ሂደትም ሐምሌ 2 ቀን 2005 እንዲጀመር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ