1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኛ ኤልያስ የጤና ችግር

ሰኞ፣ የካቲት 20 2009

ህክምናውን በጤና ጣብያ እንደሚከታተል የገለፀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ከፍ ወዳለ የህክምና መስጫ ሄዶ እንዲታከም እንዳልተጻፈለት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/2YKM2
Gambia Street in Addis Abeba, Äthiopien
ምስል picture alliance/dpa

Beri.AA (Journalist Elyas Gebru's health condition) - MP3-Stereo

ላለፉት ሦስት ወራት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአፍንጫው ጤና መታወኩን እና የተሻለ ህክምና ማግኘት አለመቻሉን ተናገረ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰረውን ኤልያስን የሚያሰቃየው የአፍንጫው አለማሽተት ችግር ያጋጠመው ከታሰረ በኋላ መሆኑን ገልጿል። ህክምናውን በጤና ጣብያ እንደሚከታተል የገለፀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ከፍ ወዳለ የህክምና መስጫ ሄዶ እንዲታከም እንዳልተጻፈለት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ