1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ኢትዮጵያን ወቀሰ

ዓርብ፣ ኅዳር 9 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን  ድረ-ገጽ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ዓለም አቀፉ  የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (cpj) ጠየቀ።

https://p.dw.com/p/2SvIn
Logo CPJ
ምስል APTN

Beri. D.C. (CPJ Report about Ethiopia 17Nov 1986) - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን  ድረ-ገጽ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ዓለም አቀፉ  የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (cpj) ትናንትና ጠየቀ። ሁለት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና አንድ ጋዜጠኛ ባለፈው ሳምንት ብቻ ኢትዮጵያ ማሰሯ ሲታወቅ አንዱን ጋዜጠኛ  እስካሁን የት እንደወሰዱት አልታወቀም ብሏል ድርጅቱ። መገናአውታሮች ከሚታፈኑባቸው ከእነ ሶሪያ፣ ኢራን  እና ቻይና ቀጥላ ኢትዮጵያ  እንደምትመደብም ድርጅቱ ገልጧል። ከአፍሪቃ ደግሞ ተወዳዳሪ የላትም ሲሉ በሲፒጄ የአፍሪቃ መርሐ-ግብር አስተባባሪ አንጄላ ኩዊንተንለዶይቸ ቬለ ገልጠዋል። ዝርዝር ዘገባውን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ