1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪኩ ጠ/ሚ በድንገት ስልጣን መልቀቅና በግሪክ የምርጫ ዝግጅት

ዓርብ፣ ነሐሴ 15 2007

የግሪክ ጠ/ሚ አሌክሲስ ሲፕራስ በፈቃዳቸዉ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸዉ በመነሳት ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።ጠ/ሚ ሲፕራስ የሥራ መልቀቂያቸዉን ትናንት ነዉ ያስገቡት።

https://p.dw.com/p/1GJb9
Griechenland Alexis Tsipras Rücktritt (Symbolbild)
ምስል picture-alliance/dpa/A. Vlachos

[No title]



ለግሪኩ ፕሬዚዳንት ፕሮኮፒስ ፓቭሎፖሎስ ያቀረቡት ከአዉሮጳ ኮሚሽንና ሌሎች አበዳሪ ሀገሮችና ድርጅቶች ጋር ለረጅም ጊዜ ሲደራደሩበት የነበረዉ ሶስተኛዉ የ 86 ቢሊዮን ይሮ የብድርና ርዳታ ፕሮግራም ፀድቆ የመጀመርያዉ ክፍያ 13 ቢሊዮን ይሮ ለመንግሥታቸዉ በተላለፈ ማግሥት መሆኑ ነዉ። ጠ/ሚ ሲፕራስ ከስድስት ወራት በፊት የግራ ኃይሎች ጥምረት ወደ ሥልጣን መንበር ሲወጡ አበዳሪ ድርጅቶች በተለይም የይሮ ተጠቃሚ ሀገሮች በግሪክ ላይ የጣሉትን አስገዳጅ የቁጠባና የኤኮኖሚ ፖሊሲ በመቃወም ሀገራቸዉን «ኔዎ ሊበራልስ» ከሚሉዋቸዉ አበዳሪዎች ጥገኝነት ነጻ እንደሚያወጡ ቃል ገብተው ነበር። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።

Griechenland Alexis Tsipras im Parlament
ምስል Getty Images/AFP/L. Gouliamaki


ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ