1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ ህዝበ ውሳኔ እቅድ ያስከተለው ውዝግብ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 23 2004

ግሪክ የአውሮፓ ህብረት ስበፈቀደላት ብድር ላይ ህዝብ ድምፀ ይሰጥበታል ካለች በኋላ ከአውሮፓ መንግሥታት ልዩ ልዩ ማስጠንቀቂያዎች እየደረሷት ነው ።

https://p.dw.com/p/Rujb
ጆርጅ ፓፓንድርዮምስል dapd

የግሪክ ህዝበ ውሳኔ ያስከተለው ውዝግብ

ትናንት ማምሻውን ፈረንሳይ ካን ውስጥ በጉዳዩ ላይ የግሪኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጅ ፓፓንድርዮን ያነጋገሩት የህብረቱ አባል ሃገራት መሪዎች ግሪክ ባላፈው ሳምንት ቃል ለተገባላት የብድርና የዕዳ ስረዛ ቅድመ ሁኔታዎች ተገዥ መሆን አለመሆኗን በአፋጣኝ እንድታሳውቅ ጠይቀዋል ። የተቀመጡትን ቅድመ ግዴታዎች ካልተቀበለችም ከብድሩ ቤሳ ቢስቲን እንደማይሰጣት አስጠንቅቀዋታል ። የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓፓንድርዮ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የተያዘውን ለመሰርዝ ዘገጁ መሆናችውን ዛሬ አስታውቀዋል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ