1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክ ምርጫ ውጤትና አንድምታው

ሰኞ፣ መስከረም 10 2008

በትናንቱ ምርጫ 35.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው ፓርቲያቸው ሲሪዛ «ነፃይቱ ግሪክ» በአህፅሮቱ Anel ከተባለው ፓርቲ ጋር ተጣምሮ መንግሥት እንደሚመሰርት ተገልጿል ።

https://p.dw.com/p/1GZyN
Griechenland Alexis Tsipras mit Panos Kammenos Koalitionsgespräche
ምስል picture-alliance/AP Photo/L. Pitarakis

[No title]

ትናንት በተካሄደው የግሪክ ምክር ቤታዊ ምርጫ ፣ለሁለተኛ ጊዜ ያልተጠበቀ ድል ያገኙት የግሪክ ግራ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሪዛ ፓርቲ መሪ አሌክሲስ ሲፕራስ ዛሬ (ማምሻውን) ቃለ መሀላ ፈፅመዋል ።(ይፈፅማሉ )ተብሎ ይጠበቃል ። በትናንቱ ምርጫ 35.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው ፓርቲያቸው ሲሪዛ «ነፃይቱ ግሪክ» በአህፅሮቱ Anel ከተባለው ፓርቲ ጋር ተጣምሮ መንግሥት እንደሚመሰርት ተገልጿል ። በእሁዱ ምርጫ ወግ አጥባቂው «አዲስ ዲሞክራሲ »28.1 በመቶ ድምፅ በማግኘት ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል ።የናዚ አስተሳሰብ የሚያራምደው «ጎልድን ዶውን» የተባለው ፓርቲ 7 በመቶ ድምፅ በማሸነፍ 3ተኛ ደረጃ አግኝቷል ። የአውሮፓ ህብረት ለሲፕራስ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክቱን አስተላልፎ ፣ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያገኙትን ሥልጣን ባለፈው ነሐሴ የተስማሙበትን የ3 ዓመት የብድርና መርሃ ግብር ተግባራዊ ለማድረግ እንዲጠቀሙበት አሳስቧል ። በእሁዱ ምርጫ ከ10 ግሪካውያን ከ4 በላይ የሚሆኑት ድምጻቸውን እንዳልሰጡ ተዘግቧል ።ስለ ግሪክ ምርጫና አንድምታው የብራሰልሱ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ