1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግራስያኒ መታሰቢያና የኢትዮጵያ አርበኞች

ዓርብ፣ ጥቅምት 30 2005

የሊቢያ «አራጅ» እና የኢትዮጵያ «ጨፍጫፊ» በመባል ለሚታወቀዉ ለማርሻል ግራሲያኒ በትዉልድ መንደሩ መታሰቢያ መሠራቱን በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ ተቃዉመዉት ነበር።

https://p.dw.com/p/16gEL
Yekatit 12 Denkmal“ in Addis Abeba, Äthiopien. Denkmal für Gefallene, die gegen Faschismus gekämpft haben Thema: „Yekatit 12 Denkmal“ in Addis Abeba. Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn_DW Schlagwörter: Addis Abeba „Yekatit 12 Denkmal
የሰማዕታት መታሰቢያምስል DW


ለቀድሞዉ የኢጣሊያ ፋሻሲት የጦር ማርሻል ለአዶልፎ ግራሲያኒ መታሰቢያ ሐዉልትና ቤተ-መዘክር መሠራቱን የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር በድጋሚ ተቃወመ። ማሕበሩ መታሰቢያዉ እንዲነሳ በሚያደርገዉ ዘመቻ የኢትዮጵያና የኢጣሊያ መንግሥታትና ሕዝቦች፥ ሌሎችም ወገኖች እንዲተባበሩትም ጠይቋል። የሊቢያ «አራጅ» እና የኢትዮጵያ «ጨፍጫፊ» በመባል ለሚታወቀዉ ለማርሻል ግራሲያኒ በትዉልድ መንደሩ መታሰቢያ መሠራቱን በተለያዩ ሐገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአደባባይ ሠልፍ ተቃዉመዉት ነበር። የኢትዮጵያና የኢጣሊያ መንግሥታት አቋም ግን በግልፅ አልተነገረም።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ