1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግራዚያኒ ሐዉልት ያስከተለዉ ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 4 2009

በአንድ ጀንበር በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ኢትዮጵያዉያንን ላስጨፈጨፈዉ የፋሺስት ጣሊያን የጦር ጀነራል ሩዶልፎ ግራዚያኒ በተወለደበት ከተማ የተሠራለት የመታሰቢያ ሐዉልት ዉዝግብ ካስነሳ ሰንብቷል። ለጀነራሉ ሐዉልት መቆም የለበትም ባዮቹ በእሱ ትዕዛዝ ወገኖቻቸዉ ያለቁባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆኑ ጣልያንያዉያንም እንደሚቃወሙት ነዉ የሚነገረዉ።  

https://p.dw.com/p/2gMIa
Benito Mussolini
ምስል AP

11.07.2017 Europe (Dispute over Gratziani statue) - MP3-Stereo

ሐዉልቱ እንዲገነባ ያደረጉት የላዚዮ ከተማ ከንቲባ እና ተባባሪዎቻቸዉም ክስ ቀርቦባቸዋል። ሐዉልቱ እንዲፈርስ ጥያቄ የሚያቀርብ የኢትዮጵያዉያን ጥምረትም ጉዳዩን በመከታተል ላይ መሆኑን ይገልጻል። ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመጪዉ ያመት ኅዳር ወር ቀጥሮታል። በጣሊያኗ አፊሌ ከተማ ተወልዶ ፋሺት ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወርር የጦር አዛዥ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ የወረራዉ ዘመን እስኪያበቃ እዚያዉ መቆየቱም ይታወሳል። ዝግጅቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ተኽለዝጊ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ