1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግራዚያኒ መታሰቢያና የኢትዮጵያውያን ቁጣ፣

እሑድ፣ ሚያዝያ 20 2005

ሚያዝያ 27 ቀን 2005 ፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች፣ በፋሺስት ኢጣልያ ላይ ድል ተቀዳጅተው ንጉሠ ነገሥቱ ከስደት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የገቡበት 72ኛ ዓመት ክብረ በዓል ይከበራል። ያለፈው ቁጭት ሳይበርድ፤ «የኢትዮጵያና የሊቢያ ዐራጅ፤ መታሪ»

https://p.dw.com/p/18O5J
ምስል picture-alliance / dpa

በሚል ተቀጣይ ስም ለሚታወቀው ፤ የፋሺስቶች መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ ቀኝ እጅ ፤ ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ከሮማ ወጣ ብሎ በላሲዮ ግዛት ፤ አፊሌ በተባለችው ከተማ፤ ባለፈው ዓመት በነሐሴ መታሰቢያ ከተሠራለት ጊዜ አንስቶ፤ ደግሞ በኢትጵያውያን ዘንድ ብርቱ ቁጣ ቀስቅሶ ነው የከረመው።

ባለፈው ሰኞ፣ ሐውልቱ የሚገኝበት ግዛት ፕሬዚዳንት ፤ ድርጊቱ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን አምነው የገንዘብ ድጋፍ እንደማይሰጥ አስታውቀዋል። በፋሺስቶች፤ ህዝቧ የተጨፈጨፈባት ፤ ቅርሶቿ የተዘረፉባት ኢትዮጵያ ፣ ለክብሯ ምን ያህል የሚገባትን አድርጋለች? ምንስ ማድረግ ይጠበቅባታል? በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ 3 የውይይት ተሳታፊዎች አነጋግረናል።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ