1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብረ ሰዶማዊነት ጥላቻ በአፍሪቃ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2007

ዩናይትድ ስቴትስ የትኛውም ግዛት ውስጥ የሚገኙ ተመሳሳይ ፆታዎች ጋብቻ እንዲፈፅሙ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር ያቀረበውን ሐሳብ የሐገሪቱ ፍርድ ቤት አጽድቋል።ባለፈው ሳምንት ደግሞ አፍሪቃዊቷ ሀገር ሞዛምቢክ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚቀጣው ህጓን አንስታለች።

https://p.dw.com/p/1FtuS
Protest gegen Diskriminierung Homosexueller in Uganda in Kenia
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

ዩናይትድ ስቴትስ የትኛውም ግዛት ውስጥ የሚገኙ ተመሳሳይ ፆታዎች ጋብቻ እንዲፈፅሙ መፍቀዷ በርካታ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል። ዩጋንዳዊው አንዲ ሙጌሻ ለምሳሌ ስለ ግብረ ሶዶማዊያን የሚሰማቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ በግልፅ አኑረዋል። «የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መፍቀድ ማለት፤ በዚህ ዓለም ላይ የኤድስ በሽታ በፍጥነት እንዲስፋፋ ፣ የአባላዘር በሽታ ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን፤ ከዚህም ሌላ ለሰው ልጆች መጨረሻ (ሞት)ነው ሲሉ ያወግዛሉ። ባለፈው ሳምንት ይህንን የዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመደገፍ ኒው ዮርክ አደባባይ የወጡትን ግብረ ሶዶማዊያንን አስመልክቶ ደግሞ ሙጌሻ « ዓለም ሀጢያትን አከበረች » ብለውታል። ሙጌሻ በዚህ አስተያየት ብቻቸውን አይደሉም፤ « ፈጣሪያችን ይርዳን፤ ትክክለኛ ትዳር ያለው በወንድ እና በሴት መካከል ነው ሲሉ ደግሞ ጆ ሙቴቤ በፁሁፍ አስፍረዋል። ቄስ ማርቲን ሴምፓ በበኩላቸው የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ማለት፤ የተፈጥሮ ሕግ የሚጣስበት እና ልጆች ከእንግዲህ የማይወለዱበት ዘመን እንደሆነ በድረ ገፃቸው ፅፈዋል።

ግብረ ሰዶማዊነትን በርካታ የዩጋንዳ ህዝብ ብቻ አይደለም የሚቃወመው የሀገሪቷ ህግም ጭምር ነው። ይሁንና እንደ ጁሌት ኪጉሊ ያሉ ተቃዋሚ ዩጋንዳዊያንም አልጠፉም። መዲና ካምፓላ የሚገኘው የማካሬሬ ዮንቨርስቲ የሳይንስ ተመራማሪ ምክንያታቸውን በጥናት ለማስደገፍ ሞክረዋል። ይህም ገና ጥንት « በድንጋይ ዘመን» መሆኑ ነው፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚያሳዩ ምስሎች ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ተገኝተዋል፤ በሚል።

Felszeichnungen der San Volksgruppe
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በድንጋይ ዘመን የተሳሉ ምስሎችምስል picture alliance/blickwinkel/McPHOTO

« እንደዚህ ሆነው የተፈጠሩ ሰዎች እዚህ አህጉር ላይም ይኖራሉ። እንደፈለጉት ሆኖ መኖር ደግሞ መብታቸው ነው፤ ምክንያቱም የሰብዓዊ መብታቸው ነው፤ ማንም መኝታ ክፍላቸው ሄዶ እንዴት እንደሚኖሩ አይመለከትም»

ይላሉ አፍሪቃዊቷ የሳይንስ ተመራማሪ ለዶይቸ ቬለ። ሳይንቲስቷ አክለውም ግብረ ሰዶማዊነት ከአንዱ ወደ ሌላኛው ሰው የሚጋባ፤ የወላጅ አስተዳደግ የሚቀይረው አልያም በህክምና የሚድን ወይም የሚመለስ ነገር አይደለም ይላሉ። ይህንን ሀሳብ ናይጄሪያዊው ኦሉዋፊሮፖ ኤዌንላ ይጋራሉ። ፔን የተሰኘው የመብት ተቆርቋሪ ድርጅት የናይጄሪያ ኃላፊ የሆኑት ኤዌንላ ፤ ናይጄሪያ በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ላይ ባለፈው ዓመት የደነገገችው የ 14 ዓመት የስር ብይን የሚመለከታቸውን ሰዎች እያሸማቀቀ ይገኛል።

«ባለፉት 18 ወራት በርካታ ሰዎች በተለይም ህዳጣን የሆኑት የናይጄሪያ ግብረ ሰዶማዊያን በከፍተኛ ፍርሃት ተውጠው እየኖሩ ይገኛሉ። በርካታ ሰዎች በተገኘው አጋጣቢ ወይ አገሩን ለቀው ጠፍተዋል፤ ወይም ደግሞ ፆታዊ ፍላጎታቸውን ሸሽገው ይገኛሉ»

የ 14 ዓመቱ እስራት ብቻ አይደለም እነዚህን ሰዎች የሚያሸማቅቃቸው ይላሉ ኤዌንላ፤ እሳቸው እንደሚሉት ጥብቁ ህግ ናይጄሪያ ውስጥ በርካታ ግብረ ሰዶማዊያን ላይ ድብደባ እና የመሳሰሉት ጥቃቶች እንዲደርስ እድል መክፈቱ ነው።

አንድ NOIP የተሰኘ የናይጄሪያ ተቋም ባቀረበው የህዝብ መጠይቅ 87 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ግብረ ሰዶማዊነትን ይቃወማል። ይህ ቁጥር ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት 92 ከመቶ ነበር። ባለፈው ዕሮብ ደግሞ ሞዛምቢክ፤ በፖርቹጊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችበት ወቅት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ላይ የደነገገችውን ቅጣት ሰርዛለች። ህጉ እነዚህ ሰዎች የግዳጅ ስራ እንዲፈፅሙ እና ስራ እንዳይሰሩ ይከለክላል፤ ከዚህም ሌላ የስነ ዓዕምሮ ሀኪም ጋር እንዲሄዱ ያዛል። ነገር ግን ሰዎች ስለ ፆታዊ ፍላጎታቸው በይፋ ስለማይገልፁ ህጉ ብዙም ተግባራ አልሆነም ነበር። ዛሬ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይፋ በማድረግ ማህበረሰቡን እናስገነዝባለን የሚሉት የዩጋንዳ እና የናይጄሪያ ተሟጋቾች ከህዝባቸው የሚያገኙት ምላሽ ግን ተቃራኒውን ነው።

Infografik Länder Afrika in denen gleichgeschlechtliche Beziehungen illegal sind Deutsch
ግብረ ሰዶማዊነት አፍሪቃ ውስጥ ህገ ወጥ የሆነባቸው ሀገራት

ዛራ ስቴፈን

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ