1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብርና ምርት ትርዒት በበርሊን

ዓርብ፣ ጥር 20 2003

አረንጓዴዉ ሳምንት የተሰኘዉ ትርዒት የታየዉ ጀርመን ዉስጥ የዶሮና የአሳማ ስጋ እንዲሁም እንቁላል ዳይዮክሲን በተባለዉ መርዛማ ንጥረ ነገር በመከሉ ብዙዉን በላተኛ ባሰጋበት ወቅት መሆኑ ነዉ

https://p.dw.com/p/QwP5
አረንጓዴዉ ሳምንትምስል dapd

የተለተያዩ ሐገራት የግብርና ምርትና ተዋፅዎች የሚቀርብበት አለም አቀፍ ትርዒት በርሊን ዉስጥ ለአንድ ሳምንት ያክል ለጎብኚ ሲታይ ሰንብቷል።በትርዒቱ ላይ ሐምሳ ሰባት ሐገራትን የወከሉ ከአንድ ሺሕ ስድስት መቶ በላይ አምራች ድርጅቶችና ኩባንዮች ተካፋዮች ነበሩ።አረንጓዴዉ ሳምንት የተሰኘዉ ትርዒት የታየዉ ጀርመን ዉስጥ የዶሮና የአሳማ ስጋ እንዲሁም እንቁላል ዳይዮክሲን በተባለዉ መርዛማ ንጥረ ነገር በመከሉ ብዙዉን በላተኛ ባሰጋበት ወቅት መሆኑ ነዉ።በትርዒቱ መሐል ዘመናዊዉን የከብቶች እርባታ የሚቃወሙ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የጀርመን ልማዳዊ ከብት አርቢዎችና ገበሬዎች የአደባባይ ሠልፍ አድርገዉም ነበር።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ