1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብጽ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

ዓርብ፣ ግንቦት 17 2004

ግብጻዉያን አንባገነን መሪያቸውን ካስዎገዱ ወዲህ ፕሬዚደታቸውን በነጻነት ሲመርጡ ውለዋል፡፡ የምርጫው ውጤት ገና ባይነገርም በመጀመሪያው ቆጠራ አስራ ሁለት ከሚደርሱት እጮዎች መካከል በርካታ አመታት ከግብጽ ፖለቲካ ተገሎ የነበረው የወንድማማች እስላሞች ፓርቲ ተመራጭ ዶር መሃመድ ሙርሲ መምራታቸውን የፓሪቲው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

https://p.dw.com/p/152gj
ምስል AP

ግብጻዉያን አንባገነን መሪያቸውን ካስዎገዱ ወዲህ ፕሬዝደንታቸውን በነጻነት ሲመርጡ ውለዋል፡፡ የምርጫው ውጤት ገና ባይነገርም በመጀመሪያው ቆጠራ አስራ ሁለት ከሚደርሱት እጮዎች መካከል በርካታ አመታት ከግብጽ ፖለቲካ ተገልሎ የነበረው የወንድማማች እስላሞች ፓርቲ ተመራጭ ዶር መሃመድ ሙርሲ መምራታቸውን የፓሪቲው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የወንድማማች እስላሞች ፓርቲ የአብዛኛው ግብጻዊ ምርጫ ከሆነ ግብጽ በሸሪያ በመተዳደር ከሳውዲ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ሀገር እንደምትሆን እየተነገረ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ግብጽ ከዚህ ቀደም ከእስራኤል ጋር ያደረገችውን ስምምነት ደግማ እንደምታጠናም ተጠቁሟል፡፡ ለአሜሪካ አውሮፓና ለጎረቤት እስራኤል የወንድማማች እስላሞች ፓርቲ እጩ መመረጥ አስደንጋጭ ዜና ነው ። በግብጽ ስለተካሄደዉ ምርጫ የሳዉዲ አረብያ የሚገኘዉን ወኪላችን ነብዪ ሲራክን አነጋግረናል።

ነብዩ ሲራክ

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ