1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፁ ፓትርያርክ ቀብር

ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2004

የሰማንያ ሥምንት አመቱ ሼኑዳ ሳልሳዊ ከግብፅ ሕዝብ አስር-በመቶ የሚሆነዉን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጥንቃቄ የመሩ ብልሕ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።በፓትሪያርኩ ሞት ፦ዛሬ በመላዉ ግብፅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ዉሏል

https://p.dw.com/p/14O9V
Coptic Pope Shenouda III leads Christmas Eve Mass at the Coptic cathedral in Cairo, Egypt, Friday, Jan. 6, 2012. This is the first Christmas since Egypt's uprising that toppled Hosni Mubarak and is the first since last year's massive explosion at a church in Alexandria, which happened under Mubarak's regime, but the culprits were never identified. Many Muslims have volunteered to protect churches in an attempt to allay fears. (Foto:Maya Alleruzzo/AP/dapd)
ሼኑዳ ሳልሳዊምስል dapd

ባለፈዉ ቅዳሜ ያረፉት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስያን ፓትሪያርክ ሼኑዳ ሳልሳዊ ዛሬ በአንድ ጥንታዊ ገዳም ዉስጥ ተቀበሩ።በካይሮዉ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተደረገዉ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት የሐገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፥ የዉጪ ሐገራት ባለሥልጣናትና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።የሽኝት ፀሎቱን የመሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳዉሎስ ናቸዉ።የሰማንያ ሥምንት አመቱ አዛዉንት ሼኑዳ ሳልሳዊ ከግብፅ ሕዝብ አስር-በመቶ የሚሆነዉን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጥንቃቄ የመሩ ብልሕ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ።በፓትሪያርኩ ሞት ምክንያት ዛሬ በመላዉ ግብፅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ሆኖ ዉሏል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ዘገባ አለዉ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ