1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፁ ፕሬዝዳት መልዕክት

ሐሙስ፣ መስከረም 17 2005

ከግብፁ ሕዝባዊ አብዮት በሕዋላ በተደረገዉ ምርጫ ሥልጣን የያዙት ሙርሲይ ኒዮርክ ለተሰየመዉ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት የበለፀጉት ሐገራት የአፍሪቃ አምባገነን ገዢዎችን መደገፋቸዉን አቁመዉ የሕዝቡን ችግር ለማቃለል ለሚጥሩት ወገኖች ተገቢዉን ድጋፍ ማድረግ አለባቸዉ።

https://p.dw.com/p/16GTp
Mohammed Morsi, President of Egypt, addresses the 67th session of the United Nations General Assembly at U.N. headquarters, Wednesday, Sept. 26, 2012. (Foto:Jason DeCrow/AP/dapd)
ሙርሲምስል AP

አፍሪቃዉያን ችግሮቻቸዉን ለማስወገድ የሚያደርጉትን ጥረት የበለፀገዉ ዓለም የመርዳት ሐላፊነት እንዳለበት አዲሱ የግብፅ ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲ አስታወቁ።ከግብፁ ሕዝባዊ አብዮት በሕዋላ በተደረገዉ ምርጫ ሥልጣን የያዙት ሙርሲይ ኒዮርክ ለተሰየመዉ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት የበለፀጉት ሐገራት የአፍሪቃ አምባገነን ገዢዎችን መደገፋቸዉን አቁመዉ የሕዝቡን ችግር ለማቃለል ለሚጥሩት ወገኖች ተገቢዉን ድጋፍ ማድረግ አለባቸዉ።ሙርሲይ አክለዉ እንዳሉት ሐገራቸዉ ፍልስጤሞች የራሳቸዉ መንግሥት ለማቆም፥ አፍሪቃዉያን ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ትደግፋለች።የዋሽግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ