1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ፖለቲካዊ ውዝግብ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2005

የግብፅ ሕዝብን በከፋፈለው አከራካሪው የሕገ መንግሥት ረቂቅ ላይ የሚካሄደው ሕዝበ ዉሳኔ በሁለት የተለያየ ቀን እና በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚደረግ የሀገሪቱ አስመራጭ ኮሚሽን አስታወቀ። ሬፈረንደሙን በበላይ የሚቆጣጠሩ

https://p.dw.com/p/170Xp
Supporters of Egypt's President Mohamed Mursi perform prayers during a rally held to show support to him in Cairo December 11, 2012. The banners read, "Yes to the constitutions!" and "Yes to the legitimacy!" REUTERS/Khaled Abdullah (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST RELIGION) // Eingestellt von wa
ምስል Reuters

ዳኞች እጥረት በማጋጠሙ ይህ ውሳኔ አስፈላጊ መሆኑን አስመራጩ ኮሚሽን አስረድቶዋል። ይኸው የዛሬ ውሳኔ ታድያ ሕዝበ ውሳኔው እንዳይካሄድ ለማከላከል ዛሬም ተቃውሞአቸውን የቀጠሉት የፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ እና የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ተቃዋሚዎች ጥረት መሳካቱን አጠራጣሪ አድርጎታል። በዚሁ መሀል ጦር ኃይሉ የሀገሪቱ መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ዳኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ ለውዝግቡ በውይይት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ አሳስቦዋል።


በግብፅ ቴሌቪዥን በተነበበው የአስመራጩ ኮሚሽን ዜና መሠረት፡ ሕዝበ ውሳኔው በፊት እንደታቀደለት የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ ስድስት እና ታህሳስ 13 እንደሚደረግ ተገልጾዋል። ሕዝበ ውሳኔው በሁለቱ ቀናት በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ይካሄዳሉ። በብዛት አክራሪ ሙሥሊሞች የተወከሉበት ሕገ መንግሥታዊ ጉባዔ ከጥቂት ቀናት በፊት ያወጣው አከራካሪው የሕገ መንግሥት ረቂቅ የሀገሪቱን ዜጎች ሁሉ መብት የማይከብር እና የማርቀቁ ሂደት ሁሉንም ያላሳተፈ ነው በሚል ብዙኃኑ ግብፃውያን ሰነዱን አለመቀበላቸውንና ካለፉት በርካታ ቀናት ጀምሮ በመዲናዋ ካይሮ የታህሪር አደባባይ እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች አደባባይ የጀመሩትን ተቃውሞ እንደሚቀጥሉ አንድ የሙርሲ ተቃዋሚ ገልጾዋል።
« ተቋሙ የሙሥሊም ወንድማማቾች ተቋም ነው። ይኸው ተቋም የሕገ መንግሥቱን ረቂቅ ከማውጣቱ በፊት ታህሪር አደባባይ ሠላም ነበር። እና አሁን ይህን ርምጃ ወስደዋል፤ የዚሁ አፀፋ ርምጃም ይኸው። »
ይሁንና፡ ሕዝቡ ተቃውሞ ብሎ ወደታህሪር አደባባይ መውጣት የጀመረው ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ሳይቃወማቸው እርምጃ መውሰድ የሚያስችላቸው ሥልጣን የሚሰጥ አወዛጋቢው ድንጋጌ ባወጡበት ጊዜ ነው። በተቃዋሚዎችና በሙርሲ ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ባለፈው ሣምንት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ፡ በዚህ ሣምንት ደግሞ በርካቶች ቆስለዋል።
ተቃዋሚዎች እንደሚሉት፡ የሕገ መንግሥት ረቂቅ የሴቶችን መብት እና የውሁዳን ሀይማኖት ቡድኖችን መብት አያከብርም።
ረቂቁን ሕገ መንግሥት ሰነድ የሚደግፉት ወገኖች፡ ለምሳሌ የሙሥሊም ወንድማማቾች አባል የሆኑት ጠበቃው መሀመድ ሰነዱ የብዙዎች ድጋፍ እንዳለው በመግለጽ ተቃዋሚዎች ቀደም ሲል ያሰሙትን ስጋት መሠረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል።
« በሬፈረንደሙ ለመሳተፍ ፈርተዋል፣ ምክንያቱም ያቀረቡትን ተቃውሞ የሚደግፍላቸው መረጃ የላቸውምና። ብዙኃኑ ግብፃውያን ከነሱ ጋ ቢሆኑና ቢደግፉዋቸው ኖሮ፡ ሕዝበ ውሳኔውን እንደማይደግፉ በድምፃቸው ሊያረጋግጡ በቻሉ ነበር። »
የፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ እና የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ተቃዋሚዎች ሕዝበ ውሳኔውን ለማከላከል ተቃውሞአቸውን እንደሚቀጥሉ ቢያስታውቁም፡ ጥረታቸው የሚሳካ እንደማይመስል ታዛቢዎች ገልጸዋል። የፖለቲካው ቀውስ ይበልጡን እንዳይካረር የሀገሪቱ ጦር ኃይል ዋና አዛዥ እና የመከላከያ ሚንስትር ጀነራል አብደል ፋታህ አል ሲሲ ፕሬዚደንት ሙርሲ እና የተቃዋሚ ወገኖች፡ ዳኞች እና የክርስትያንና ሙሥሊም ሀይማኖት አባቶች በዛሬው ዕለት ተገናኝተው ለውዝግቡ በውይይት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ አሳስቦዋል። ባለፈው ሣምንት የሕገ መንግሥቱ ረቂቅ እስካልተሻረ ድረስ ከሙርሲ ጋ ለመወያየት ፈቃደኛ ያልነበረው ዋነኛው የተቃዋሚዎች ጥምረት በዛሬው ውይይት የመሳተፍ ያለመሳተፉን ጉዳይ ገና እያጤነው መሆኑን የብሔራዊ መድን ግንባር አመራር አባል እና የነፃ ግብፃውያን ፓርቲ መሪ አህመድ ሰይድ አስታውቀዋል።የግብፅ ዜና ወኪል ሜና እንዳስታወቀው፡ በ 150 የውጭ ሀገራት የሚገኙ ከ 500,000 የሚበልጡ ግብፃውያን በየሚኖሩበት ሀገር ወዳለው የግብፅ ኤምባሲ በመሄድ በረቂቁ ሕገ መንግሥት ላይ ድምፃቸውን መስጠት ጀምሮዋል።

An Egyptian expatriate living in Lebanon casts her vote in a referendum on the new Egyptian constitution at the Egyptian embassy in Beirut December 12, 2012. Egyptians abroad went to embassies on Wednesday to vote in a referendum on the new constitution that President Mohamed Mursi fast-tracked through an Islamist-led drafting assembly, drawing the ire of the opposition. REUTERS/Sharif Karim (LEBANON - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል Reuters
Two Egyptian men ride a motorbike past a tank stationed outside the presidential palace in Cairo on December 12, 2012. Egypt's powerful army has called for President Mohamed Morsi and the secular opposition to meet later in the day to stop a crisis over an imminent constitutional referendum from tearing the country apart. AFP PHOTO/MARCO LONGARI (Photo credit should read MARCO LONGARI/AFP/Getty Images)
ምስል Marco Longari/AFP/Getty Images
A family of anti-Mursi protesters hold signs reading, "Leave! No constitution" in Tahrir Square in Cairo December 11, 2012. Nine people were hurt when gunmen fired at protesters camping in Cairo's Tahrir Square on Tuesday, according to witnesses and the Egyptian media, as the opposition called for a major demonstration it hopes will force President Mohamed Mursi to postpone a referendum on a new constitution. REUTERS/Mohamed Abd El Ghany (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ