1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎሚስታ ሠራተኛው ወጣት ህይወት

Lidet Abebeቅዳሜ፣ ኅዳር 25 2008

ቢኒያም ተስፋዬ የሚሠራበት ቦታ ሁሌ ጫጫታ እና ግርግር አይጠፋም። ደንበኞቹ መኪናቸው ላይ እክል የገጠማቸው አሽከርካሪዎች ናቸው። በአዲስ አበባ የአንድ የጎሚስታ ሠራተኛ ህይወት ምን ይመስላል? ቢኒያም የግል ህይወቱን አጫውቶናል።

https://p.dw.com/p/1HGt9
Äthiopien Addis Abeba Autowerkstatt Binyam Tesfaye
ምስል Hilina Abebe

የጎሚስታ ሠራተኛው ወጣት ህይወት

ቢኒያምን በስልክ ሳገኘው፤ አዲስ አበባ ውስጥ ተቀጥሮ በሚሠራበት ጎሚስታ ኤሌክትሪክ ስላልነበረ ሥራ አቋርጦ ነበር። ይሁንና ደንበኛ ስለሚመጣ ግርግሩ አልተቋረጠም። አሁን በሚሠራበት ከተማ ተወልዶ ያደገው ቢኒያም መጀመሪያ የቧንቧ ሠራተኛ ነበር ነገር ግን የመኪና ጎማ ሥራ ላይ ለመሠማራት ወሰነ። በተለይ የመጀመሪያ የጎሚስታ የሥራ ቀኑን በደንብ ያስታውሳል።
ቢኒያም ሥራ የሚጀምረው ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ ነው። ይህም እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ይቀጥላል። «ህይወት ብዙ ውጣ ውረድ የተሞላች ናት» ይላል ።በቀን ለ12 ሰዓታት ቢሠራም አብዛኛውን ጊዜ ገቢዉ ከእጅ ወደ አፍ ናት።
የቢኒያም ሥራ ከበርካታ ሰዎች ጋር ያገናኘዋል። እንደ ሰውም ፤ ለወጣቱ ያላቸው አመለካከት ይለያያል። «ቢኒያም በትምህርቱ ያን ያህል አልገፋሁበትም» ይላል። እስከ 10ኛ ክፍል ነው የተማረው።
አዲስ አበባ ውስጥ በጎሚስታ ሥራ ላይ ስለተሰማራው ወጣት ቢኒያም ተስፋዬ የበለጠ ለመስማት የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ