1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎርደን ብራውን ፈተና

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001

በብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን የሚመራው የሌበር ፓርቲ ሰሞኑን በታሪኩ ታይቶ የማይታወቅ ሽንፈት ተደራርቦበታል ።

https://p.dw.com/p/I6Pb
...የጀመርኩትን ሳልጨርስ ?ሙጥኝ...ምስል AP

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአካባቢና የማዘጋጃ ቤቶች ምርጫ ጥቂት ድምፅ ያገኘው ሌበር ባለፈው ሳምንት መጨረሻው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ደግሞ ታይቶ የማይታወቅ ክስረት ነው የደረሰበት ። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን በገንዘብ ሚኒስትርነታቸው ዘመን የተደነቁ ቢሆንም የዛሬ ሁለት ዓመት ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ግን የአመራር ችሎታቸው ጥያቄ ውስጥ ወድቋል ። የሌበር ፓርቲ አባላት ብራውን ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቅ ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ድልነሳ ጌታነህ / ሂሩት መለስ /ሸዋዬ ለገሠ