1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎርጎሪዮሣዊው ገና በዓል

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 16 2007

የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎሮጎሮሳዉያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተለዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ዛሬ ተከብረ። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የሐይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች ለየተከታዮቻቸዉ መንፈሳዊና ዓለማዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/1EA83
Papst Weihnachtssegen 25.12.2014
ምስል AFP/Getty Images/A. Pizzoli

1,2 ቢሊዮን ሕዝብ መንፈሳዊ አባት የሆኑት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ «ኡርቢ ኤታ ኦርቢ» (ለከተማዉና ለዓለም) በተሰኘዉ ዓመታዊ መልእክታቸዉ ተከታዮቻቸዉ ለችግረኞች በተለይም ለስደተኞች እንዲራሩ መክረዋል። የሰባ-ስምንት ዓመቱ መንፋሳዊ አባት እንዳሉት ዓለም ሰብአዊነትና ርሕራሔን ትሻለች።

ገና በቫቲካን
ገና በቫቲካንምስል REUTERS/Giampiero Sposito

«ለኛ የቀረቡንን ወገኖችን መከራና ችግር ለማቃለል ፅናቱና ርሕራሔዉ አለን? ወይስ ዉጤታማ ግን ሰብአዊነት የጎደለዉና ፍቱኑን ቃለ-እግዚአብሔርን ጋር የሚቃረን መፍትሔ እንመርጣለን።ዓለም ዛሬ ምን ያሕል ርሕራሔን ትሻለች።»ርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከአፍቃኒስታን እስከ ደቡብ ሱዳን፤ ከእስራኤል-ፍልስጤም እስከ ሁለቱ ኮንጎዎች የሚካሔደዉን ጦርነት፤ የኢቦላን ሥርጭት እና በሕፃናት ላይ የሚፈፀመዉን በደል በየተራ አዉስተዉ ዓለም ብዙ እንባዎች እፈሰሱባት ነዉ ብለዋል። የጀርመን ፕሬዝዳንት ዩአኺም ጋዉክ በበኩላቸዉ ሕዝባቸዉ ጠብ ጥላቻን አስወግዶ በመቻቻልና መፋቀር አብሮ እንዲኖር ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና ባሕል ፀረ-ሰላምን፤ ጥላቻንና ጠብን አይቀበልም።

Glühwein
ምስል Fotolia/juniart

«ባሕላችንና ዴሞክራሲያችን ፀረ-ሰላምን፤ ጥላቻንና ሕይወት የሚያጠፋ አመፃን የሚቃወም ነዉ። ሰበአዊነት የተላበሠ ማሕበረሰብ በየዕለቱ አንዱ ለሌላዉ ደሕንነት መቆሙን እና አንዱ ከሌላዉ ደሕንነት ጋር መኖሩን የሚያስተዉል ነዉ።በተሟላ ሠላም በጋራ መኖር የሚቻለዉ በዚሕ መንገድ ብቻ ነዉ።ሁሉም ሐይማኖቶች የሚያስተምሩት፤ ሁላችንንም የሚያስተሳስረንና የሚያስገድደንም ይኸዉ ነዉ።

በተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት የሚገኙት ወኪሎቻችን የላኳቸውን ዘገባዎች ያድምጡ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ