1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቁ

እሑድ፣ ሐምሌ 17 2008

በጎንደር እና አካባቢዉ ከሰሞኑ የተቀሰቀሰዉ አለመረጋጋት ለጊዜ አሁን መስከኑን የሚያመለክቱ እንዳሉ ሁሉ፤ ችግሩ ተዳፈነ እንጂ ዉጥረቱ አልሰከነም የሚሉም አሉ።

https://p.dw.com/p/1JUXq
Fasil Schloss Gonder Äthiopien
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

የጎንደሩ አለመረጋጋት

በጎንደር አለመረጋጋቱም ሆነ ፍጥጫዉ እንዲከሰት ጥያቄያቸዉን በሰላማዊ እና ሕጋዊ መንገድ ለሚመለከታቸዉ የመንግሥት አካላት ያቀረቡ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት መታሰር ወይም የኮሚቴዉ አባላት እንደሚሉት ደግሞ ባልታወቁ ኃይሎች መታፈን ዋናዉ ምክንያት ነዉ። መንግሥት በበኩሉ ችግሩ የተከሰተዉ በሕጋዊ ጥያቄ ሽፋን የኢትዮጵያን ሰላም እና ልማት ለማደናቀፍ ከኤርትራ መንግሥት ጋር የሚላላኩ ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ ይናገራል። የሰዉ ሕይወት መጥፋትንም ሆነ የንብረት ጉዳትን ያስከተለዉ ይህ ዉጥረት ወደ ብሔር ግጭት እንዳያመራ ስጋታቸዉን የሚገልፁ አሉ።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ «ኦዲዮውን ያዳምጡ» የሚለውን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ