1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ መለስ ዜናዊ ጋዜጣዊ መግለጫ

ዓርብ፣ ጥር 8 2001

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዛሬ የብሄራዊ አንድነት መድረክን ከከፈቱ በኋላ ለዓለም አቀፍ ዜና አውታር ጋዜጠኞች በተመድ የስብሰባ ማዕከል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።

https://p.dw.com/p/GZE8
የጠቅላይ ሚንስትር መለስ
ጠቅላይ ሚንስትር መለስምስል AP Photo

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሶማልያ እየወጣ ያለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ተልዕኮውን እንዳሳካ ማመናቸውን አስታውቀዋል። በሶማልያ የተፈለገውን ያህል ሰመረጋጋት ባይሰፍንም፡ ሰላም እንዲመጣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሳይጠቀምበት በመቅረቱ ተፈጥሮ የነበረውን ዕድል ጥቅም ላይ እንዳልዋለ አስረድተዋል። ከኤርትራ ጋር ስላለው ውጥረት ሁኔታና ዛሬ በአዲስ አበባ ስለተከሰተ ፍንዳታም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

ታደሰ እንግዳው