1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጤንነት ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2004

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ታመው ቤልጅየም መዲና ብራስልስ በሚገኝ ሴይንት ሉክ በተባለ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን በኢንተርኔት የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/15ZF7
Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi is seen at his offices in the capital, Addis Ababa, Wednesday, Jan. 10, 2007. Zenawi said Wednesday that a U.S. airstrike in Somalia had not killed any civilians and, in his opinion, would not help create an Iraq-style insurgency or hinder efforts to build a peacekeeping force in the country. (AP Photo/Les Nauheus)
ምስል AP

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በአዲስ አበባ በይፋ አለመታየታቸው፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይትም ሆነ ትናንት በተጠናቀቀው የአፍሪቃ ህብረት ጉባዔ ላይ አለመገኘታቸው ብዙ እያነጋገረ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ በአዲስ አበባ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፤ በብራስልስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተያየት ለማግኘት በኢሜይል ብንጠይቅም ዜናው ውሸት እና የተሳሳተ ነው በሚል ያቀረብነውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። በመሆኑም፡ ብራስልስ የሚገኘው ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በዚያ ሕክምና እያደረጉ ነው ስለመባሉ በበኩሉ የሰማው እንዳለ ጠይቄው ቀጣዩን መልስ ሰጥቶኛል።

ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ