1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ መለስ ንግግርና የህዝብ አስተያየት

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2003

በትናንትናዉ ዕለት ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን ያካሄደዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመጪዉ ዓመታት ፓርቲያቸዉ ያቀዳቸዉን የልማት ተግባራት አስመልክተዉ ሰፊ ንግግር አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/PDmb

በንግግራቸዉ ከፊታችን አምስት ዓመታት በኋላ አገሪቱ የምግብ ርዳታ እንዳማትፈልግ፤ በቀጣይ ዓመታት ደግሞ መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገራት ተርታ እንደምትሰለፍ፤ በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ረገድም ከፍተኛ ለዉጥ እንደምታሳይ ጠቁመዋል። ንግግራቸዉን የተከታተሉት አንዳንድ ወገኖችን ወኪላችን በማነጋገር አስተያየታቸዉን እንደሚከተለዉ አሰባስቦ ልኮልናል፤

ታደሰ እንግዳዉ፤ ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ