1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጡት ማጥባት ሳምንት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2001

አዲስ እናቶችን ለልጆቻቸዉ እንዴት ጡት ማጥባት እንዳለባቸዉ ማስተማር ቢያንስ የ1,3ሚሊዮን ህፃናትን ነፍስ ሊታደግ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት WHO ይናገራል።

https://p.dw.com/p/J4Gu
...ከጡጦ ይልቅ ጡት...ምስል BilderBox

በዓለም ዙሪያ ቁጥራቸዉ በመቶ ሲሰላ ከ40በመቶ በታች የሚገመቱ እናቶች ብቻ አራስ ልጆቻቸዉን እስከ ስድስት ወር ጡት እንደሚያጠቡም የWHO መረጃዎች ይጠቁማሉ። የጤና ድርጅቱ እንደሚለዉ አብዛኞቹ እናቶች ለልጃቸዉ እንዴት ጡት ማጥባት እንዳለባቸዉ ባለማወቃቸዉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በሚሰማቸዉ ህመም ምክንያት ማጥባትን ይተዋሉ። WHO ከሐምሌ 25እስከ ነሐሴ 1 ቀን ድረስ የጡት ማጥባት ሳምንት ብሎ ሲያስብ፤ ዓላማዉ የእናት ጡት በወጉ ያላገኙ ህፃናት ለበሽታ የመጋለጥ እድላቸዉ የሰፋ መሆኑን ለማስገንዘብ ነዉ።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፤ ሸዋዬ ለገሠ፣

ተክሌ የኋላ