1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጡት ካንሰር ቅድመ ጥንቃቄ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 11 2007

ቀደም ባሉ ዓመታት የበለፀጉት ሃገራት በሽታዎች ተብለዉ ከሚፈረጁት ካንሰር አንዱ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተዉ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የኗኗር ሁኔታ መለወጥን ተከትሎ በአዳጊና ደሀ ሃገራትም መስፋፋቱ ይታያል።

https://p.dw.com/p/1DZPn
Gentest zu Brustkrebs bei Myriad Genetics Inc
ምስል AP

በያዝነዉ የጥቅምት ወር በተለያዩ ሃገራት ሰዎች ስለጡት ካንሰር መንስኤና ምንነት አዉቀዉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ይደረጋል። የጡት ካንሰር በአብዛኛዉ ሴቶችን የሚያጠቃ ይሁን እንጂ ወንዶችም ሊያጋጥማቸዉ ይችላል።

በየዕለቱ ለግማሽ ሰዓት ያህል በእግራቸዉ የሚጓዙ ሴቶች የጡት ካንሰርን ስጋት ሊቀንሱ እንደሚችሉ ጥናቶች ያመለክታሉ። በተለይም የወር አበባ ዑደት ካቆመ በኋላ የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴዎችን ካዘወተሩ በበሽታዉ የመያዝ እድላቸዉ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ጥናቱ ጠቁሟል። ጥናቱን ያከናወኑት የፈረንሳይ የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉትም በብዙዎቹ ላይ እንደታየዉ መደበኛና ተከታታይ እንቅስቃሴ የሚያድርጉ ሴቶች በጡት ካንሰር የሚያዙበት አጋጣሚ መቀነሱን አስተዉለዋል። ለዚህም ነዉ ሌሎች የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንኳ ባይሳካ በእግር ለ30 ደቂቃ ያህል በቀን መጓዝ ከበሽታዉ ሊታደግ እንደሚችል ያመለከቱት። ኢትዮጵያዊዉ የዘርፉ ባለሙያና ሃኪም ዶክተር ቦጋለ ሰሎሞንም ስለበሽታዉ የሰጡን ማብራሪያ ይህንኑ ያጠናክራል። ዶክተር ቦጋለ የጡት ካንሰርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ምክንያቶችን በትክክል ይኽ ነዉ ብሎ ለመወሰን እንደሚያዳግት በመጠቆም ለበሽታዉ ሊጋልጡ ይችላሉ የሚባሉትን ያብራራሉ። ሴቶች ብቻ አይደሉም የጡት ካንሰር ሰለባዎች፤ ቁጥራቸዉ ከመቶ ሲሰላ ይቀንስ እንጂ ወንዶችንም አይምርም።

Gesundheit Gesundheitswesen Medizin Früherkennung Brustkrebs
በየወሩ ሊደረግ የሚገባዉ ፍተሻምስል Fotolia/Forgiss

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ